Thursday, May 19, 2016

አማራውን በማፈናቀል ወንጀል የሚፈለጉት የቤንሻንጉል ጉምዝ ርእሰመስተዳደር አቶ አህመድ ናስር ከዚህ ዓመት በሞት ተለዩ፡፡ May 19, 2016 – ምኒሊክ ሳልሳዊ — Comments

አማራውን በማፈናቀል ወንጀል የሚፈለጉት የቤንሻንጉል ጉምዝ ርእሰመስተዳደር አቶ አህመድ ናስር ከዚህ ዓመት በሞት ተለዩ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አህመድ ናስር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩአማራውን በማፈናቀል ወንጀል የሚፈለጉት የቤንሻንጉል ጉምዝ ርእሰመስተዳደር አቶ አህመድ ናስር ከዚህ ዓመት በሞት ተለዩ፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አህመድ ናስር ከዚህ ዓመት በሞት ተለዩ፡፡
የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሃብታሙ ታየ ዛሬ ለኢዜአ እንዳስታወቁት አቶ አህመድ ናስር ከ2001 ዓ.ም. ጀምሮ ክልሉን በርዕሰ መስተዳድርነት መርተዋል ፡፡የከልሉ ገዥው ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) በምክትል ሊቀመንበር መርተዋል፡፡
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በእርሻ ምህንድስና፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በቻይና ሆሃ ዩኒቨርሲቲ በውሃ ምህንድስና የተከታተሉት አቶ አህመድ ናስር በአሁኑ ወቅት የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር በቀድሞው ግብርና ገጠር ልማት ሚኒስትር ዴኤታነት አገልግለዋል፡፡በቅንነትና በታማኝነት ሲያገለግሉ መቆያታቸውን ሃላፊው አመልክተዋል ፡፡በተለይ ተበታትኖ የሚኖረውን የክልሉን ህዝብ በመንደር በማሰባሰብ ውጤታማ ለማድርግ በተደረገው የመጀመሪያው የክልሉ እድገትና ትረንስፎርሜሽን እቅድ እንዲሁም አሁን በመተግባር ላይ በሚገኘው ሁለተኛውን እቅድ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በግንባር ቀደምትነት መርተዋል፡፡
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብቻ ሳይሆን በደቡብ ክልል ሸበዲኖ እና ሃዋሳ ወረዳዎች በግብርና ባለሙያነት ሠርዋል፡፡በ1957 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ ጠዴቻ መልካ ቀበሌ የተወለዱት አቶ አህመድ ናስር የክልሉን ህዝብ በክልል ምክር ቤትና በፌዴሬሽን ምክር ቤት ወክለው በቅንነት አገልግለዋል፡፡ባደረባቸው ህመም በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ህክምና ሲረዱ ቆይተው በ51 ዓመታቸው ትናንት ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡አቶ አህመድ ባለትዳርና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበሩ፡፡የቀብር ስነ-ስርዓታቸው ቤተሰቦቻው ፣ወዳጅ ዘመዶቻው ፣የስራ ባልደረቦቻቸው እና የክልሉ ህዝብ በተገኘበት በአሶሳ ከተማ እንደሚፈጸም ተገልጾአል፡፡

No comments:

Post a Comment