Thursday, May 19, 2016

ማንም ከማንም በላይ አይደለም::የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሁሉ የፌዴራሉ ቋንቋ ቢሆኑ ማንም የሚጠላ የለም:

ኢትዮጵያዊነት ማለት ፍቅር ነው:;ኢትዮጵያዊነት ማለት አንድነት ነው::ኢትዮጵያዊነት ማለት የማይላቀቅ ክቡር መንፈስ ነው::ብዙ ማለት ይቻላል ስለ ኢትዮጵያዊነት… ኢትዮጵያውያን እኩል መብት እኩል ሃገር እኩል ተጠቃሚነት ሊኖራቸው ይገባል::ማንም ከማንም አያንስም::ማንም ይሁን ማንም በአንድነት ስም ሊጫን የሚፈለግ ግዞት አሊያም በአንድነት ስም ሕዝቦችን ቅኝ ለመግዛት የሚፈለግ ከሆነ አደጋው የከፋ ነው::በአንድነት ስም ተደብቆ የጎሳ ፖለቲካን ለማጦዝ አሊያም የሌላውን ኢትዮጵያዊ ጥቅም ቀብሮ የአንድን ብሄር ብቻ ለማራገብ መሞከር ይህም ውሎ ይደር እንጂ የከፋ አደጋ አለ::ኢትዮጵያዊነት በዘመነ-ወያኔ አመጣሹ የጎሳ ፖለቲካ እና የጎሳ ፌዴራሊዝም በቂም ለማኖር የሚጥሩ ያልበሰሉ ፖለቲከኞች በጥላቻ ለመሙላት ቢጣደፉም አልተሳካላቸውም::
ኢትዮጵያ እጅግ በርካታ ብሄረሰቦች እና ቈቋዎች በስፋት የሚነገሩበት ውብ ሃገር ናት::በፍቅር እና በአንድነት በመከባበር እና በመተሳሰብ የኖረን ሕዝብ በጎሳ ፌዴራሊስም ተብትቦ ለመበታተን ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ያልተቧጠጠ ጉድ የለም:: በአሕጉራችን የብቸኛ ፊደል ባለቤት የሆነውን አማርኛ እንደ ቅኝ ገዢዎች ቋንቋ አድርጎ ለማሳየት በመሞከር የቋንቋ ብጥብጥ ለመፍጠር የሚጥሉ ጭፍኖች ዛሬም ድረስ እየለፈለፉ ይገኛሉ::በሃገሪቱ የሚነገሩ እንደ አማርኛ ኦሮሚኛ ጉራጊኛ ሱማሊኛ ትግሪኛ እና የመሳሰሉት በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ቋንቋዎች በመላው ሃገሪቱ የመንግስት መጠቀሚያ ቢሆኑ በየትምህርት ቤቱም ቢሰጡ ማንም የሚተላ የለም::እንኳን ኢትዮጵያዊ ቋንቋዎችን ይቅርና ተነጮችን ቋንቋ ከፍለን እንማር የለም እንዴ ?
ጥቂቶች በዘረኝነት የተጀቦኑ ግለሰቦች የብሄራቸውን ቋንቋ ብቻ አተልቀው የልላውን ለመደፍጠጥ የሚያደርጉት ሙከራ በፍጹም አይሳካም::በየማህበራዊ ድህረገጹ መጻፍ እና መሬት ላይ አውርጄ እተገብራለሁ ማለት የተለያየ እና የማይገንኝ ሲሆን መልሱም በባዶ ውጤት መመለስ ነው::በመጀመሪያ የሕዝቦችን እኩልነት ልንቀበል ይገባል::በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሄሮች ባህል ቋንቋ እና ተውፊት ሁሉ የራሳችን አድርገን ልንቀበል ይገባል::የሌላውን ሳናከብር የኛ የሚያከብርልን የለም:: ተጽእኖ ፈጥረን መላ እናመጣለን ብሎ ማሰብ አደጋው የሚተርፈው ለራሱ ለሚንቀዥቀዠው አካል ነው::አሁንም የምለው ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ነው::ማንም ከማንም በላይ አይደለም:: የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሁሉ የፌዴራሉ ቋንቋ ቢሆኑ ማንም የሚጠላ የለም::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.

No comments:

Post a Comment