Sunday, May 29, 2016

የሕወሓት ባለስልጣናት ከአደባባይና መድረክ ለመደበቅ የወሰኑ ሲሆን ቀጣዩ የደህንነት ተቋሙ አሰራር ላይ መከሩ

የሕወሓት ባለስልጣናት ከአደባባይና መድረክ ለመደበቅ የወሰኑ ሲሆን ቀጣዩ የደህንነት ተቋሙ አሰራር ላይ መከሩ

 የደህንነት ተቋሙ አሰራር በአዲስ መልክ ሊቀየር መሆኑ ተሰምቷል::አዲሱ አሰራርን በተመለከተ ጥናት መጀመሩን እና በደህንነት ተቋሙ ውስጥ ከሕወሓት አባላት ውጪ ሌሎች የሚኖራቸውን ሚና የሚገድብ መሆኑ ታውቋል::እንዲሁም ወታደራዊ ደህንነቶች መበርከት ስላለባቸው አዳዲስ ሰልጣኞችን በመሰብሰብ በሰራዊቱ ውስጥ ሊነሱ የሚችሉ ችግሮችን ማውደም እንደሚቻል ታሳቢ ተደርጎ አዳዲ ወታደራዊ ደህነቶች በጦላይ ስልታና እንዲሰጣቸው እንዲሁም የወታደራዊ ደህነት መኮንኖች እስራኤል እና ሩሲያ ሄደው እንዲሰለጥኑ አስፈላጊው ስራ እንዲሰራ ተወስኗል::ወታደራዊ ጄኔራሎች በሳምንት ውስጥ ብቻ ከደህንነት ተቋሙ ባለስልጣናት ጋር ከዚህ ቀደም በተሻለ በተከታታይ እየተገናኙ በሃገሪቱ ላይ የሚነሱ ችግሮች የክልል ባለስልጣናትን በማስቀደም በእንጭጩ በፍጥነት እንዲቀጩ ተወስኗል::
የግንቦት ሃያን የወያኔ በዓል ተከትሎ የሕወሓት ባለስልጣናት ወደ አደባባይ መውጣትን ሊቀንሱ ይገባል የሚለው ሃሳብ ላይ መመከሩ ለደህንነት ቢሮ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ገልጸዋል::በዚሁ የምክክር ስብሰባ ላይ አደባባይ ላይ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ እስካልተገኘ ድረስ ከፍተኛ የሕወሓት ባለስልጣናት ሕዝብ ፊት ሳይታዩ ከጀርባ ሆነው ስራ ለመስራት ተነጋግረዋል::በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ጥላቻ እያተረፍን ነው የሚል እደምታ ያለው አጀንዳ የተነሳበት ይህ ምክክር ከሙስና እና ከግድያ እንዲሁም ከእስር ጋር በተያያዘ በስፋት እጅ የሚጠቆመው በሕወሓት ባለስልጣናት ላይ እንጂ በሌሎች የኢሕኣዴግ አባል እና አጋር ድርጅቶች ላይ ስላልሆነ እንዲሁም የግንባሩ ድርጅቶች አባላት ሳይቀሩ እጃቸውን ሕወሓት ላይ መጠቆም እንደደረሱ በምክክሩ ላይ መተማመን ላይ ተደርሷል::ከዚህ ቀደም ከክልል ባለስልጣናት ይሁን ከፌዴራል ባለስልጣናት ጀርባ የሕወሓት ባለስልታናት እንዳሉ ቢታወቅም አሁን የታሰበው ለየት የሚያደርገው ግን በረቀቀ መልኩ ለማዘዝ የክልል ባለስልጣናትን ለመወንጀል መዘጋጀታው ነው::
ማንኛውንም ጉዳዮች በማስፈጸም እና በመተግበር ስራ ላይ ሊሰማሩ ይገባል ተብለው የታጩት በሃይለማርያም የሚመራው የደቡብ ድርጅት አባላት ሲሆኑ እንደ ኦሕዴዽ እና ብአዴን እስጥ ያሉ ሰዎች በጥንቃቄ ክትትል እየተደረገባቸው የሕወሓት ባለስልጣናትን ትእዛዝ እንዲፈጽሙ እንዲሁም ማንኛውም ትእዛዝ ለአንድ በክልል ይሁን በፌዴራል ለተመደበ ባለስልጣን ከሕወሓት ሰዎች በቃል ብቻ እንዲወርድ ተደርጎ ምስጢር እንዲጠብቅ እና አፈጻጸሙን እንዲተገብር ማበረታቻ ገንዘብ በማጉረስ ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ ማድረግ እንደሚቻል ከስምምነት ተደርሶበታል::በሕዝብ ዘንድ ማጉረምረም ቢከሰት ወዲያው ባለስልጣኑን በማሰር አሊያም በመቀየር እንደሁኔታው ወቅታዊ ትኩሳቶችን የተከተለ እርምጃ በልጥሎች እንዲወሰድ እንደሚደረግ ተመክሮበታል::የሕወሓት ባለስልጣናት ከዚህ ቀደም እንደሚያድርጉት ፊትለፊት ድንፋታ እና ፊትለፊት በመጋፈጥ ማዘናጋት ማጭበርበር የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው እና ሕዝቡ እንደነቃ በምክክራቸው ላይ ከመተማመን መድረሳቸው ራሳቸውን ቀስ በቀስ ከሕዝብ መድረኮች በማሸሽ እና ጉዳያቸውን በትእዛዛቸው መሰረት ከሚፈጽሙት ጀርባ ሆነው ከቀደድሞው በተለየ በረቀቀ መልኩ ሊተገብሩ ተስማምተዋል::ቀጣዩ የፕሮፓጋንዳ ስራ የሚሆነው የፖለቲካው ስልጣኑ ከሕወሓት ሰዎች ውጪ እንደሆነ አድርጎ ሕዝብን ማሳመን እንዲሆን ይደረጋል:: 
Minilik Salsawi's photo.

No comments:

Post a Comment