Tuesday, May 24, 2016

ኢትዮጵያና የሲአይኤ ሴራ (ኤርሚያስ ቶኩማ)


የ1981ን መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ካካሄዱት ጀነራሎች መካከል በሕይወት የተረፈው ብርጋዴር ጀነራል ቁምላቸው ደጀኔ ብቻ ነው አተራረፉ በርካታ መላ ምቶችን የፈጠረ ቢሆንም ትክክለኛ የሲአይኤ ኤጀንት እንደነበረ መረጃዎች ያመላክታሉ። አሜሪካ ምስራቅ አፍሪካን ለመቆጣጠር ከነበራት ተስፋ የተነሳ ለመንግሥቱ ኃይለማርያም እና ለስርአቱ ከፍተኛ ጥላቻ ነበራት በዚህም የተነሳ ሻእቢያና ህወሀትን ከመርዳት አልፋ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በጥቅም በመደለል የደርግ ስርአትን በማፍረስ ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር በርካታ ጥረቶችን አድርጋለች።
አሜሪካ ከመለመለቻቸው የሲአይኤ አባላት መካከል አንዱ ብርጋዴር ጀነራል ቁምላቸው ደጀኔ ነው። ቁምላቸው ደጀኔ የ1981ን መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከጓደኞቹ ጋር ሲያደርግ ከአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ድጋፍ ይደረግለት ነበር ሆኖም መፈንቅለ መንግሥቱ ከሽፎ ጀነራሎቹ ሲገደሉ ቁምላቸው ደጀኔ ሊያመልጥ ችሏል። እንዴት አመለጠ? ብርጋዴር ጀነራል ቁምላቸው መፈንቅለ መንግሥቱ እንዳልተሳካ ሲያውቅ ለአሜሪካ ኤምባሲ በማሳወቅ የአሮጊት ልብስ ወደጉራጌ ዞን በመሄድ በመደበቅ ከሲአይኤ የሚመጣውን መረጃ መጠበቅ ጀመረ እንደአጋጣሚ ሆኖ በወቅቱ የአሜሪካን ኮንግረስ ማን የነበሩት ሚኪ ሊላንድ በኢትዮጵያ የሚገኘውን የስደተኞች ካምፕ ለመጎብኘት ወደኢትዮጵያ ባቀኑበት የሚጓዙበት አውሮፕላን ጫካ ውስጥ ይከሰከሳል የተከሰከውን አውሮፕላን ለመፈለግ የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያ መንግስትን አስፈቅዶ አራት ሄሊኮፕተሮች ወደኢትዮጵያ ይልካሉ።
ከተላኩት አራት ሄሊኮፕተሮችን መካከል ሦስቱ የሚኪ ሊላንድን አውሮፕላን እንዲፈልጉ ሲታዘዙ አንደኛው ሄሊኮፕተር ግብ ወደጉራጌ ዞን በማምራት ብርጋዴር ጀነራል ቁምላቸውን ይዞ ወደኬንያ ናይሮቢ እንዲበር ተልእኮ ይሰጠዋል እንደታዘዙትም ሶስቱ ሄሌኮፕተሮች የአውሮፕላኑን ስብርባሪ ሲፈልጉ አንደኛው ሄሊኮፕተር ብርጋዴር ጀነራል ቁምላቸውን ይዞ ወደኬንያ በረረ። አሜሪካም የሲአይኤ ምስጢርን በዚህ አይነት ስትደብቅ ቁምላቸውም የአሜሪካ ዜግነት ተሰጥቶት አሜሪካ መኖር ጀመረ። አሜሪካ ዛሬ ፍላጎቷ ሞልቶላት እንደፈለገች የምታዘው መንግሥት በኢትዮጵያ አንግሳ የአሜሪካንን መንግሥት የተቃወመውን አልሻባብን በኢትዮጵያውያን ወታደሮች ነፍስ ትዋጋለች አሜሪካ በገንዘብ እኛ በጉልበት አልሻባብን እንዋጋለን። አሜሪካ በአሁኑ ወቅት በየትኛውም መስፈርት የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን የመርዳት ፍላጎት የላትም ምክንያቱም የህዝቡን ፍላጎት ጉድጓድ ከቶ የአሜሪካን መንግሥትን ጥቅም ለማስከበር የቆመ ኢህአዴግን የመሠለ ፓርቲ በኢትዮጵያ አንግሳለች። #ኤርሚያስ_ቶኩማ

1 comment: