Thursday, May 19, 2016

“እኔ ዘረኛ አይደለሁም !”

“እኔ ዘረኛ አይደለሁም !”

Yidnekachew Kebede's photo.
“እኔ ዘረኛ አይደለሁም !” —–
በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ 15ኛ ተከሳሽ የሆኑት፡፡አቶ አግባው ሰጠኝ “እኔ ዘረኛ አይደለሁም፣ፍጹም ዘራኛ በሆኑ የማረሚያ ቤት አስተዳደሮች እና ጥበቃዎች “አማራ” ነህ እያሉ ስቃይና እንግልት እያደረሰብኝ ነወ፡፡” በማለት በከፍተኛው ፍርድ ቤት 10ኛ ችሎት ያቀረብት አቤቱታ ነው፡፡ አቶ አግባው ሰጠኝ እንደገለጹት ከሆነ ፣ መጋቢት 16 ቀን 2008 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት፣በማረሚያ ቤት እየደረሰባቸው ስላላው እንግልትና ስቃይ ፣አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ ብናቀርብም እስካሁን የተሰጠን ምንም ዓይነት ምላሽ የለም ያሉ ሲሆን፡፡
በዛሬው ዕለት ማለትም ግንቦት 11 ቀን 2008 ዓ.ም ፣በከፍተኛው ፍርድ ቤት በድጋሚ ያቀረብት አቤቱታ “በማረሚያ ቤቱ ባሉ ኃላፊዎች በፖለቲካ አመለካከቴ ብቻ ሰብአዊ መብቴ እየታጣሰ ነው፡፡ በማረሚያ ቤቱ ፍጹም ዘረኝነት በተጠናወታቸው ሰዎች ጥበቃ ሥር ነው ያለሁት፣እኔ ዘረኛ አይደለሁም ነገር ግን በአማራነቴ ብቻ ተጽኖ ተደርጎብኛል፡፡ በቤተሰቦቼ እና በጓደኞቼ እንዳልጠየቅ ክልከላ እየተደረገብኝ ነው፡፡ በተጨማሪ በጨለማ ቤት ብቻዬን እንደሚያስሩኝ ዛቻና ማስፈሪሪያ አድርሰውብኛል፡፡”በማለት ለፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን ያቀረቡ ሲሆን፡፡ፍርድ ቤቱ አቶ አግባው ያቀረቡት አቤቱታ ከዳመጠ በኋላ በጠበቃቸው አማካኝነት ፣በጹሑፍ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
በዚህ መዝገብ 4ኛ ተከሳሽ የሆኑት፣ ለፍርድ ቤቱ ያቀረብቱ አቤቱታ” ማረሚያ ቤቱ ገንዘብ አዋጡ እያለ የስገድደናልን “በማለት አቤት ያሉ ሲሆን፤ጉዳዩን አንደገለጹት ከሆነ፣”እኛ እስረኞች ነን፣ነገር ግን በየክፍላችን እየመጡ የጥበቃ ብር አዋጡ ይሉናል፣ይሄ ነገር እንዴት ይሆናል በማለት ለማረሚያ ቤቱ አሰተዳዳር ጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ መግኘት አልቻልንም፡፡ይባስ ብለው ገንዘብ ማዋጣት ካልቻላችሁ በጉልበት ሥራ ማካካስ አለባችሁ ብለው ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡ፍርድ ቤቱ ይህን አቤቱታችን ሰምቶ ተገቢውን ትእዛዝ “ይስጥልን ያሉ ሲሆን፡፡ፍርድ ቤቱ የማረሚያ ቤቱ አሰተዳደር ተወካይ በጉዳዩ ዙሪያ የጠየቀ ሲሆን ተወካዮ ፣የመለሱት መልስ” እኔ ስለተባለው ነገር የማውቀው ነገር የለም አጣራለሁ “በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ላይ የሚገኙት፣ 15 ተከሳሾች ላይ ብይን ለመስጠት የመጨረሻ ቀጠሮ ለነሐሴ 13 ቀን 2008 ዓ.ም ሰጥቷል፡፡

No comments:

Post a Comment