ተቃዋሚዎች የስልጣን ጥመኞች ናቸው …. ቢሆኑማ ኖሮ …
#Ethiopia #EPRDF #EthiopianOppositionparties #MinilikSalsawi #Change
#Ethiopia #EPRDF #EthiopianOppositionparties #MinilikSalsawi #Change
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ሰሞኑን ወያኔዎች በሕዝብ እና ሃገር ሃብት ላይ የሚቀልዱት እያንገበገበን ለውጥ ፈላጊ ነን ባይ የማህበራዊ ድህረገጽ አሸብሻቢዎችም አብረው ቀልዱን ሲያሳምሩለት ማስተዋል በጣም ያማል:: ሕወሓት መራሹ አገዛዝ እና ካድሬዎቹ ለለውጥ የሚታገሉትን ሃይሎች የስልጣን ጥመኞች እንደሆኑ አድርገው ሲስሉ ይስተዋላል::አብዛኛውን ጊዜ ስለሃገር አንድነት እና ፍቅር ሲወራ የቀድሞ ስርዓት ናፋቂ ብለው የሚፈርጁት ሕወሓቶች ተቃዋሚውን የስልጣን ጥመኛ ብለው የጭቃ ጅራፋቸውን ሲያጮኹት ይውላሉ:: ተቃዋሚዎችን የስልጣን ጥመኞች ቢሆኑ ኖሮ ስለ ሕዝብ ነጻነት እና መብት አገራቸውን ጥለው ባልተሰደዱ አልያም በሃገር ቤት ያሉ ከስራቸው ባልተፈናቀሉ ባልታሰሩ …የተወሰኑ ምሳሌዎች ብንወስድ …..
ከሃገር ቤት ዶክተር መረራ ጉዲና እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲሁም ከውጪው ከተሰደዱት ውስጥ ዶክተር ብርሃኑ ነጋና መሰሎቻቸውን መመልከት በቂ ነው::ከነዚህ የለውጥ መሪዎች ጋር የተያያዙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሉ:: በምሳሌ ደረጃ ስማቸውን ከላይ የጠቀስኳቸእ የስልጣን ጥማት ቢኖራቸው ኖሮ ዶክተር መረራ የአዲስ አበባን ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንትነት ጋዜጠኛ እስክንድር የሚዲያ ሚኒስትርነት ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እስከ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት መድረስ ይችሉ ነበር:: ሌሎችም የተሰደዱ የታሰሩ የሚንገላቱም የተገደሉም እንዲሁ…ወያኔ ጉያ ውስጥ ከሕዝብ ይልቅ ለሆድ ማደር ከተቻለ ስልጣን ማግኘት ቀላል ነው::ተቃዋሚዎች በአላማ ጽናት ለሕዝብ ነጻነት ና መብት መታገላቸው ስራቸው ብቻ ምስክር ይሆናቸዋል:: የተቃዋሚው ሃይል የስልጣን ጥመኛ ቢሆን ኖሮ ይህን ያህል መንገድ እየተሽከረከረ አይንገላታም አይገደለም አይታሰርም አይሰደድም ነበር:: ጭንቅላት ያልፈጠረባቸው የሕወሓት ካድሬዎች ይህንን ቀላል አስተሳሰብ ደጋግመው በማውራት የበታችነታቸውን እያሳዩን ይገኛሉ::
የውሸት ጎተራው ሕወሓት ተቃዋሚዎችን ለመፈረጅ የሚጠቀምበት ጉዳይ ሁሉ የተበላበት እቁብ ነው::ተቃዋሚዎች የስልጣን ጥማቱ ቢኖራቸው ኖሮ በአቋራኝ የተፈለገበት የስልጣን እርከን ላይ መድረስ ይችላሉ::ይህ ደግሞ በሆድ አደሮች እና በታማኝ ተቃዋሚዎች በፊትለፊት እያየነው ያለነው ጉዳይ ነው::ተቃዋሚዎችን የስልጣን ጥመኞች ማለት በራስ እኩይ ስራ ውስጥ ራስን ለመደበቅ የሚደረግ ሩጫ ነው::የስልታን ጥመኞች እነማን ናቸው የሚለውን ለመለየት ስልጣንን ሙጥኝ ብለው ሃገር በመዝረፍ አለቅም ያሉት የወያኔ ባለስልጣናት እና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ስልጣኑን ለሕዝብ ያስረክቡ::የስልጣን ጥመኝነት ያለበት ምንጊዜም በስልጣን ላይ ያለ አካል ነው::የስልጣን ጥማት ያለበት አምባገነን አገዛዝ ብቻ ነው!!!#ምንሊክሳልሳዊ
No comments:
Post a Comment