Monday, May 16, 2016

Hiber Radio: አገዛዙ በአርባምንጭ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይን ልጃችሁ ሞቷል ብሎ ካረዳ በኋላ መረጃው ሐሰት በመሆኑ ቤተሰብ ከለቅሶ ተነሳ – ወጣቶች እየታፈሱ ነው

የህብር ሬዲዮ ግንቦት 7 ቀን 2008 ፕሮግራም
<...በአገር ቤት በጋዜጠኝነት ሙያዬ በተንቀሳቀስኩባቸው ቦታዎች ሁሉ በተለይም ፕሬዝዳንት ኦባማ መጥተው ከሄዱ በሁዋላ ጫናው እየበረታ ሄዷል።በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በጋዜጠንነት ሙአ ውስጥ ያለ ሰው ሕይወቱ አደጋ ላይ ነው። እስካሁን ባለው ሁኔታ በጫና ውስጥ ሆኜ ለመስራት ሞክሬያለሁ አሁን ግን ሁኔታዎች ከዚያ እየከፉ ሄዱ...ከአገር ከመውጣቴ በፊት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ውብሸት ታዬን ዝዋይ ሄጄ አይቻቸሁ ነበር። ተመስገን ሞራሉ ልበ ሙሉነቱ አሁንም አብሮት ቢሆንም በሌላ በኩል ግን ሕይወቱ አደጋ ላይ ነው። አብረውት ያሉትን እስረኞች በሙሉ በማስነሳት አጠገቡ ሁለት የመከላከያ ሻምበሎችና አንድ የደህነት አባል አለ። በእስር ቤት በአንዷለም አራጌ ላይ የተፈጸመውን ስታይ... . በቅርቡ ከአገር የተሰደደው ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ጋር ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን አድምጡት)<...ረዳት አብራሪ ሐይለመድን አበራ በነጻ ተብሎ በአገሪቱ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተፈርዶለታል። ብዙ ጊዜ የሕግ የበላይነት ሲባል ይሄው ነው።በነጻ ፍርድ ቤት ቀርበህ ተከራክረህ ፍትህ ስታገኝ። በአገሩ ያ ባለመኖሩ በሌለበት አስራ ዘጠኝ ዓመት ከስድስት ወራት ተፈርዶበታል።እዚህ ደግሞ ነጻነቱ በፍርድ ቤት ውሳኔ ተረጋግጧል። በእርግጠንነት የምነግርህ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሁዋላ ከእስር ቤት ወጥቷል።ነጻ ነው...የፍርድ ቤቱ ውሳኔውን በሌላ መንገድ ለመዘገብ የሞከሩት የተሳሳተ ነው ረዳት አብራሪ ሐይለመድህን አበራ ነጻነህ ተብሎ ተፈረደለት እንጂ አልተፈረደበትም። ከዚህ ቀደም የፍርድ ቤቱ ጉዳይ ስላለ የኢሚግሬሽን የስደተኝነት ጥያቄው አይነሳም ነበር። አሁን ግን ፍርድ ቤት ነጻነቱን ስላረጋገጠለት ቀጣዩ ሂደት ያ ነው ...> አቶ ጴጥሮስ አሸናፊ ከስዊዘርላንድ ስለ ረዳት አብራሪ ሐይለመድን አበራ አንዳንዶች የተለየ ትርጉም የሰጡትን ትክክለኛውን የፍርድ ቤት ውሳኔና ወቅታዊ የረዳት አብራሪውን ሁኔታ አብራርቶልናል (ሙሉውን ያዳምጡት)
ሁበር የዋጋ አሽከርካሪዎች የዋጋ ማስተካኬአ እንዲያደርግ ጥአቄ አቅርበውለት በቅርቡ ዋጋ አስተካክላለሁ ማለቱና በሌሎች የሁበር ተወካዮች እና የአሽከርካሪዎች ስብሰባ በተመለከተ ቃለ መጠይቅ ከአቶ ፍቅረስላሴ ወልደየስ የሙሉ ጊዜ ሁበር አሽከርካሪ ጋር የተደረገ ቆይታ(ሙሉውን አድምጡት)
ድርቅ፣ሰደት፣መፈናቀል ፣ጎርፍ እና ሞት እያመሰው ያለው ወቅታዊው የኢትዮጵያ እና የሕዝቧ ችግሮች ሲዳሰሱ (ልዩ ዘገባ))
የኢሳት ስድስተኛ ዓመት ዝግጅትን በተመለከተ በቬጋስ ከአዘጋጅ ኮሚቴው ጋር ያደረግነው ቃለ ምልልስ
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሕይወት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑ ተገለጸ
ሊገድሉትም ሆነ ሊመርዙት ይችላሉ የሚል ስጋት አለ
በአርባ ምንጭ አካባቢ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ጥቃትን ተከትሎ በከተማዋ በርካታ ወጣቶች እየታሰሩ ነው
አገዛዙ ልጃችሁ ሞቷል ብሎ ያረዳቸው የአንድ አርበኛ ቤተሰብ መረጃው ሀሰተና መሆኑን አውቀው የጀመሩትን ለቅሶ አቁመዋል
አቶ ሐይለማሪአም ደሳለኝ ሱዳን ከኤርትራ ጋር እንድታስታርቃቸው እንደሚሹ ተናገሩ
ኢትዮጵያዊው ወጣት አክቲቪስት እና ጦማሪ በእስር ቤት ውስጥ ከደረሰበት ድብደባ ሳያገግም በአገዛዙ ፍርድ ቤት የአምስት ዓመት እስራት ተፈረደበት
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አባት አሰልጣኝ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ አረፉ
አዲሱ የለንደን ሙስሊም ከንቲባ አሜሪካዊ እጩ ፕ/ታዊ ተወዳዳሪ ዶናል ትራምፕን ስለ እስልምና ታላቅነት ሊያስተምሯቸው እንደሚፈልጉ ተናገሩ
የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ እስር ቤት ሳለ አስከሬንህ እንደ ፕ/ር አስራት ወልደየስ ከእስር ቤት ይወጣል መባሉንና ተደጋጋሚ በደል በእስር ቤት እንደተፈጸመበት ገለጸ
ለሕዝቡ ሚታገሉ ሲታሰሩ ቤተሰቦቻቸው እንዳይጎዱ መታሰብ እንዳለበት ጠቀሰ
ኢትዮጵያ አንድ የኬኒያ ኩባንያ ሀብት የሆነ ከሁለት ሚሊዮን በላይ በመያዣነት አገተች
ድርጊቱ የዲፕሎማሲ ቻና በአዲስ አበባ ገዢዎች ላይ ሊአሳድር ይችላል ተብላል
የሕወሓት-ኢህአዴግ መንግስት ሰሞኑን ከግንቦት ሰባት ማረኳቸው ብሎ ለሕዝቡ አሰራጨው የጦር መሳሪአዎች ምስል የተሳሳተ መሆኑ ተጋለጠ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ

No comments:

Post a Comment