Tuesday, May 24, 2016

የግንቦት 20 በዓል ግዳጁ ጦፏል::የሆስፒታል ሰራተኞች በሽተኞች ላይ በር ዘግተው ለፌሽታ ሊሰበሰቡ ነው::

ሃገር በኢኮኖሚ ቀውስ ሕዝብ በረሃብ እየተቸገረ ወያኔ ለጋሾችን እየለመነ ባለበት በዚህ አደገኛ ወቅት ላይ የግንቦት ሃያ በዓልን ለማክበር ከፍተኛ ገንዘብ በየቦታው እየፈሰሰ ሲሆን በረሃብ የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት ከ1.4 ቢሊዮን ብር ወደ 1.5 ቢሊዮን ብር እርዳታ እንደሚያስፈርግ ተመድ እየተናገረ ነው ወያኔም እየለመነ ነው::የግንቦት 20ን የኢሕኣዴግ 25ኛ አመት በዓል አስመልክቶ በየመንግስት መስሪያ ቤቱ በግዳጅ ተሰብሰቡ እየተባለ ሲሆን የመስሪያ ቤቶች የሰዓት መቆጣጠሪያ መፈረሚያ መዝገብ ሳይቀር ተገዶ ወደየመሰብሰቢያ አደራሽ እንደሚሄድ ታውቋል:: የግንቦት 20 ኢሕኣዴጋዊ በአል በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በሚል የተጠራው የግዳጅ ስብሰባ ላይ ሁሉ የቀረ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት በየመስሪያ ቤቱ የተለጠፉ ማስታወቂያዎች ይጠቁማሉ::
የፓርቲ በዓልን ለማክበር በግዳጅ እየተጠሩ ያሉ ዜጎች በስብሰባ ላይ የማይገኙ ከሆነ እስከ አሸባሪነት ክስ ሊመሰረትባቹ ይችላል የሚል በካድሬዎች በውስጥ ፕሮፓጋንዳውን ያጧጧፉት ሲሆን በየሆስፒታሉ ያሉ ሰራተኞች ለስብሰባው ቅድሚያ በመስጠት በሽተኞች ላይ በር ዘግተው ለፌሽታ እንዲሰበሰቡ መገደዳቸውን ጠቁመዋል::ግዳጁን የማይፈጽሙ ከሆነ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ስለተዛተባቸው የነጻነት መብታቸውን አገዛዙ እየተጋፋ እንደሆነ በመናገር ላይ ናቸው:: ‪#‎



No comments:

Post a Comment