Tuesday, May 31, 2016

በምስራቅ ጎጃም ጎዛምን ወረዳ አራት ሰው ተገደለ!! አደገኛ ውጥረት እንደነገሰ የአካባቢው ሰዎች ገለፁ፡፡


በምስራቅ ጎጃም ጎዛምን ወረዳ አራት ሰው ተገደለ!! አደገኛ ውጥረት እንደነገሰ የአካባቢው ሰዎች ገለፁ፡፡
በምስ/ጎጃም ጎዛምን ወረዳ ደንበል ቀበሌ ትላንት ግንቦት22/09/08 ዓ ም መለስተኛ የጦር ግንባር ሆኖ አረፈደ የወረዳው የፖሊስ ደህንነት ጨምሮ ሁለት ሚሊሻ የሞቱ ሲሆን ገዳዩም እራሱን አጠፋ ሲሉ ከወደ ጎጃም የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡===//

ቀደም ባለ ጊዜ የመከላኪያ ሰራዊት አባል በመሆን ለ14አመት ሲያገለግል የቆየው እና በራሱ ፍቃድ ከነበረበት ኃላፊነት የለቀቀው አቶ ይሄነው ትርፌ ምክንያቱ በውል ሳይታወቅ በትላንትናው ዕለት ግንቦት 22/09/08/ዓ ም ከጠዋቱ 1ሰዓት መኖሪያ ቤቱ በወረዳው ፖሊስ ደህንነት እና ሁለት በታጠቁ የሚሊሻ አባሎች ተከቦ እጅ እንዲሰጥ ቢጠየቅም የለም-አይሆንም! አላደርገውም! ያለው አቶ ይሄነው ትርፌ በያዘው መሳሪያ ጦርነት ተከፍቶ እስከ እረፋዱ 6ሰዓት በቶክስ እሩምታ ጎዛምን ስትናወጥ አረፈደች በማለት የሚገልፁት የአካባቢው እማኞች የወረዳው ፖሊስ አዛዥ አቶ ግዛቸው ጨምሮ የሚሊሻ አባሉ አቶ ገደፋው ቢያዘኝ እንዲሁም ልጅ አየነ የተባሉት ታጣቂዎች ለሕልፈተ ሕይወት የተዳረጉ ሲሆን የሶስቱን መሳሪያ የጨበጠው አቶ ይሄነው ትርፌ በመጨረሻም እራሳቸውን በያዙት መሳሪያ እንዳጠፉ ከአካባቢው የአይን እማኞች በደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከጥቂት ሰዓት በኃላ ተጨማሪ ኃይል በቦታው ቢደርስም አራቱም ሰዎች በሕይወት አልነበሩም፡፡ በዚህ ወቅት አንድ ወታደር በሞተው አቶ ይሄነው ትርፌ ላይ ሁሉት ጥይት መተኮሱ ሁኔታ ያስገርማል ሲሉ የመረጃው ምንጭ ይናገራሉ፡፡ ጎዛምን በአሁኑ ሰዓት ውጥረት መኖሩ ስጋት ፈጥሮባቸው ይገኛል፡፡
Sintayehu Chekol
Hanan Ahmed's photo.

No comments:

Post a Comment