Tuesday, May 24, 2016

ሰማያዊ ፓርቲ በውስጥ ጉዳዩ ውሳኔ አሳለፈ !


ሰማያዊ ፓርቲ በውስጥ ጉዳዩ ውሳኔ አሳለፈ !
#Ethiopia #Semayawiparty #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በቅርቡ በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ የታየውን አጠቃላይ ችግር አስመልክቶ፤ የብሔራዊ ምክር ቤት፣ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን እና የብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ግንቦት 14 ቀን 2008 ዓ.ም በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ ችግሩን ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሳባ፣ የምክር ቤት አባላት፣ የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን እና የስራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በተካሄደው ስብሰባ፣ በፓርቲው ውስጥ የተፈጠረው ችግር ደረጃ በደረጃ የፓርቲውን መዋቅር እና መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በማድረግ በአስቸኳይ ችግሩ እንዲፈታ ተወስኗል፡፡
የሰማያዊ የፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች፤ ችግሩን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በማገዝ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን፣ ፓርቲው የሚጠበቅበትን መደበኛ ሥራ በአግባቡ እንዲወጣ ውሳኔ አሰልፏል፡፡ #ምንሊክሳልሳዊ
ግንቦት 16 ቀን 2008 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment