ግንቦት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ዜና (May 18, 2016 NEWS)
# የወያኔው የድህንነት መስርያ ቤት ሹም የነበረው የእስር ቅጣት ተበየነበት
# የዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት ያልተወራረደ ሂሳብ ያለባቸው የመንግስት መ/ቤቶች መኖራቸውን ገለጸ
# ጌታቸው አምባዬ አዲሱን የጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዲመራ ተሾመ
# በናይጀሪያ የሰራተኞች ማህበር ሰራተኞች
# በሊቢያ በአንድነት መንግስቱ ስር ያለው ኃይል ቁልፍ የሆነ ቦታ ከአይሲስ አስለቀቀ
# በደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት ረብሻ ተነሳ
ዝርዝር ዜናዎች

የመጣለትን በጭበጨባ የቀረበለትን በጩኸት በፉጨት መቀበልና ማጽደቅ መለያ የሆነው የወያኔ ፓርላማ አዲስ ያዋቀረውና በፈረሰው የወያኔ ፍትሕ ሚኒስትር ምትክ የተቋቋመው የጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ቢሮን እንዲመራ የፈረሰው የወያኔ ፍትህ ሚኒስትር የነበረው ጊታቸው አምባዬ የወያኔ ጠቃላይ ዐቃቤ ሕግ ተብሎ በወያኔ መሾሙና በፓርላማው መጽደቁ ታውቋል። የወያኔ ቡድን ምክንያቱ ባልተገለጸ ሁኔታ የፍትህ ሚኒስትሩን በጠቅላይ አቃቤ ህግ ከተካ ወዲህ ሚኒስትሩን መልስ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግነት ማስቀመጡ የወያኔ መሪዎች ቀደሞውና ፍትህ የሚያውቀውን ሚኒስትር መስሪያ ቤታቸውን ለሕግና ለደንብ እንደገዛ ሳይሆን የበለጠ ፍትህ እንዲረገጥ ሚዛን እንዲዛባ ለማድረግ በማሰብ መሆኑን ስም እንጅ የተለወጠና የተቀየረ ነገር እንደሌለና እንደሚኖር የሕግ ባለሙያዎች በእርገጠኛነት ይናገራሉ።

በናይጄሪያ የነዳጅ ዋጋ በ 67 ከመቶ እንዲጨምር መደረጉን በመቃወም ሁለት ታላላቅ የሰራተኛ ድርጅት ማህበሮች ጠቅላላ የስራ ማቆም አድማ ለዛሬ ለሮብ ግንቦት 10 ቀን 2008 ዓም ጠርተው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ያደረገው ማገጃ ሁለቱን ማህበሮች የከፋፈለ መሆኑ ታውቋል። መንግስት የነዳጅ ዋጋ በአሁኑ ወቅት ከሚሸጥበት .43 ዶላር በሊትር ወደ .72 ዶላር በሊትር ከፍ ለማድረግ የወጠነውን እቅድ በመቃወም የናይጄሪያ ሌበር ኮንግሬስ እና የትሬድ ዩኒየን ኮንግሬስ የሚባሉ ሁለት ታላላቅ የሰራተኛ ማህበሮች ከረቡዕ ግንቦት 10 ቀን ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ለማካሄድ አቅደው እንደነበር ይታወቃል። ከናይጄሪያ የፍርድ ሚኒስትር የቀረበውን የአቤቱታ ሰነድ ተቀብሎ አንድ የናይጄሪያ ፍርድ ቤት ጉዳዩ በድርድር እስኪያልቅ ድረስ የስራ ማቆም አድማው እንዲነሳ የወሰነውን ውሳኔ ትሬድ ዩኒየን ኮንግሬስ የተባለው የሰራተኛ ማህበር የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተቀብሎ ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው እንዲሄዱ መመሪያ ሲያስተላልፍ የናይጄሪያ ሌበር ፓርት የተባለው ግን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አልደረሰኝም በሚል አድማው እንዲቀጥል አዟል። መንግስት ለፍርድ ቤት ባቀረበው ሰነድ ላይ ማህበሮቹ ስራ ለማቆም የሚያስችላቸው ትክክለኛ መንገድ ያልተከተሉ መሆናቸውን እቅዳቸውን በቅድሚያ ለመንግስት ያላቀረቡ መሆናቸውን ይገልጻል። የስራ ማቆም አድማው በስራ ላይ የሚውል ከሆነም የናይጄሪያ መንግስት በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያጣ መሆኑን ከፍተኛ የጸጥታ ችግር ውስጥ እንደሚገባ ይገልጻል። በዛሬው ቀን የተደረገ የስራ ማቆም አድማ ስለመኖሩና አለመኖሩ ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ወቅት ድረስ የተገኘ መረጃ የለም። በሌላ ዜና ከሁለት አመት በፊት በቦኮሃራም ከተጠለፉት ወደ 200 ከሚሆኑት ልጃገረዶች መካከል አንደኛዋ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘቷ ረቡዕ ዕለት የዜና ምንጮች ገልጸዋል። ዝርዝሩን እንደንደደረሰን እናቀርባለን።
ለአንድነት መንግስት ታዛዥ የሆነ የሊቢያ ጦር ቀደም ብሎ በአይሲስ ኃይሎች ተይዞ የነበረ አቡ ግሬን የተባለውንና ሁለት ታላላቅ መንገዶች የሚገናኙበትን ቁልፍ ቦታ ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓም. ከአይሲስ ኃይሎች አስለቅቆ የያዘ መሆኑን ገልጿል። ይኸው ጦር በተጨማሪም አይሲስ ወደ ተቆጣጠራትና በርካታ ኃይሎች በማስፈር ወታደራዊ ይዞታውን አጠናክሮ ወደ ሚገኝባት ሰርት ወደተባለችው ከተማ እየገሰገሰ መሆኑ ተነግሯል። የሊቢያ አንድነት መንግስት የአይሲስ ኃይሎችን ለመደምሰስ ተዋጊ አይውሮፕላኖች እንዲሰጡት የምእራብ መንግስታትን ጠይቋል። ከሁለት ቀን በፊት አሜሪካ ጣሊያንና ሌሎች መንግስታት ቪየና ላይ ባደረጉት ስብሰባ ቀደም ብሎ የተጣለው ማዕቀብ ተነስቶ ለሊቢያ አንድነት መንግስት ሰራዊት ወታደራዊ ስልጠናና የመሰሪያ እርዳታ ለማድረግ መስማማታቸው ይታወሳል።
ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት ውስጥ ፕሬዚዳንት ዙማ ለፓርላማው አባላት ንግግር ለማድረግ ሲዘጋጁ የኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተርስ የሚባለው ፓርቲን በምክር ቤቱ ውስጥ የሚወክሉ የሆኑ ወደ 20 የሚሆኑ የምክር ቤት አባላት ፕሬዚዳንቱ እንዳናገሩ በጩኸት ለማገድ በመሞከራቸው ከፍተኛ ረብሽና ግርግር ተከስቶ እንደበር ለማወቅ ተችሏል። የጸጥታ ኃይሎች ሰዎችን ከምክር ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ለማስወጣት ባደረጉት ሙከራ የቦክስ ድብድብ እንደነብርም ታውቋል። ፕሬዚዳንት ዙማ የመንግስት ገንዘብ አለአግባብ በማውጣትና በሌሎች ክሶች በተደጋጋሚ ጉዳያቸውን የደበብ አፍሪካ ፍርድ ቤቶች በተደጋጋሚ የቀረበ ሲሆን በአንዳንዶቹ ላይ የተፈረደባችወ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ምክንያት በተቃዋሚዎቻቸውና እርሳቸው በሚመሩት የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግሬስ በአንዳንድ አባላት ጭምር ተቀባይነት ያጡ ቢሆንም አብዛኛቹ የፓርቲ አባላት ድጋፍ ስለሰጧቸው በስልጣን ሊቆዩ እንደቻሉ ይታወቃል። ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን ከፓርላማው መሰብሰቢያ አዳራሽ በፖሊስ ተገፍተው የወጡት የተቃዋሚው የ ኢኮኖሚ ፍሪደም ፋይተርስ ፓርቲ መሪ የአገሪቱ ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲወገዱ ለማድረግ ፓርቲያቸውን የጀመረውን ትግል የሚቀጥሉ መሆናቸውን ለጋዘጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።
የቀድሞ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር ቤምባ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ የጠየቀ መሆኑን የዜና ምንጮች ገለጹ። ከአስራ አራት ዓመት በፊት መፈንቅለ መንግስት ለማክሸፍ በሚል ሰብበ ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ተልኮ የነበረው ሚስተር ቤምባ የሚመሩት የአማጺ ኃይል በሕዝብ ላይ በፈጸመው ግድያና ሴቶችን አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ባላፈው መጋቢት ወር በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ክስ የቀረረባችው መሆኑ ይታወሳል
No comments:
Post a Comment