Tuesday, May 17, 2016

የማእከላዊ ማሰቃያ በሕወሓት ገራፊዎች የተደፈሩ ሴቶች ለስለልቦና ችግር እየተጋለጡ ነው:


የማእከላዊ ማሰቃያ በሕወሓት ገራፊዎች የተደፈሩ ሴቶች ለስለልቦና ችግር እየተጋለጡ ነው::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Maekelawiprison‬ ‪#‎WomenPrisoner‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በሕወሓት አባላት ብቻ በሞኖፖል የሚተዳደረው የአገዛዙ ዜጎችን በተለይ የለውጥ ፈላጊ ሃይሎችን በከፍተኛ ደረጃ የሚሰቃዩበት የማእከላዊ የማሰቃያና የቶርች የጨለማ እስር ቤት የሚገኙ ሴት እስረኞች በሕወሓት የገራፊ ቡድን አባላት እየተደፈሩ ለስነልቦና ችግር እየተጋለጡ መሆኑን ወደ ቂሊንጦ የተዘዋወሩ እስረኞች ገለጸዋል::
Minilik Salsawi's photo.
ወደ ቂሊንጦ የተዘዋወሩ እስረኞች እንደሚናገሩት በርካታ ሴት እስረኞች በማእከላዊ ማሰቃያ ማእከል ውስጥ ተደፍረው ለከፍተኛ የስነልቦና ችግር መዳረጋቸውን በቅርቡ ከአርሲ ታፍና የመጣችውን ሃዋ ተብላ የምትታወቅ ወጣት ሴት በመድፈር ለከፍተኛ የአእምሮ ችግር ዳርገዋታል ሲሉ አጋልጠዋል::በማእከላዊ ያሉ ሴት እስረኞች አብዛኛዎቹ ፍርድ ቤት ያልቀረቡና በጨለማ ቤት ተዘግቶባቸው ከቤተሰብ ጋር የማይገናኙ በሕወሓት የገራፊዎች ቡድን አባላት ከፍተኛ የወሲብ ጥቃት የሚደርስባቸው መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የተከታተሉ የቂሊንጦ አዳዲስ እስረኞች ገልጸዋል::
ከዚህ ቀደም የተለያዩ ሴት እህቶቻቸን ላይ የደረሰውን አስደንጋጭ እና አሳዛኝ ቶርች ከፍተኛ የስቃይ እና የመከራ እስር በተመለከተ በማእከላዊ ማሰቃያ ማዕከል ታስረው የነበሩ ከጻፉት ምስክርነት ለማንበብ ችለናል::አለምኣቀፍ የእስረኞች ጉዳይ የተመለከተ ስራ የሚሰራ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ዘጠና ሶስት ሺህ እስረኞችን በማሰር ሁለተኛ ስትሆን ከባለፈው አመት በአስራ ስምንት ሺህ እድገት ማሳየቷ ሲጠቆም ይህ ቁጥር በጦር ካምፖች ውስጥ በማእከላዊ ማሰቃያ ጣቢያ አዲስ አበባ ደብረዘይት ናዝሬት መቀሌ ባዶ ስድስት ደብረብርሃን መንገድ አለባቸው ጫካ በሚገኙ 153 የደህንነት ድብቅ እስር ቤቶዎች በተሃድሶ እስር ቤቶች እና ጨለማ ቤቶች እንዲሁም በግለሰቦች ቤት ውስጥ የታሰሩትን ኢትዮጵያውያን በሪፖርቱ አላካትተም:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment