Sunday, May 15, 2016

በሲኤምሲ ያሉ ነዋሪዎች ቤታችን እየፈረሰ ነዉ አሉ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች | 
  • 898
     
    Share
CMC
BBN news May 14, 2016
በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ ዘጠኝ በሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ቤታችን ፈርሶ ያለመጠለያ እየቀረን ነዉ ሲሉ ቅሬታ አሰሙ። በሰዉ አገር ተሰደን ያጠራቀምነዉ መና ቀረ የሚሉት የሲኤምሲ ነዋሪዎች አሉ። የህይወት መስዋእትነት ከፍለዉ የተሰደዱ የቤተ ሰብ አባላቶቻችን በላኩልን ገንዘብ የገነባነው ቤት ያለምንም ርህራሔ ፈረሰብን ወገን ይድረስልን በማለት የጥሪ ድምጻቸዉን ያሰሙም አሉ። ድሆች አዝነዋል። ያለ ረዳትና ደጋፊ ባዶ ቀረን የሚሉ አቅመ ደካሞች ቢቢኤን ድምጻችንን ለአለም ያሰማልን ሲሉ ተማጽነዋል።
መንግስት ለድሃ ዜጎቹ እርዳታና ጥበቃ ማድረግ ሲገባዉ ቤታቸዉን በላያቸዉ ላይ እያፈረሰ ለአደጋ እያጋለጻቸዉ መሆኑን በምሬት ይገልጻሉ።
የወረዳዉ ባለ ስልጣናት ገንዘብ መክፈል የሚችለዉን ነዋሪ ገንዘብ እየተቀበሉ ሲያልፉ ገንዘብ መክፍል የማይችለዉ ድሃው ነዋሪ እቃዉን እንኳ ማዉጣት ሳይችል በላዩ ላይ ቤት እየፈረሰበት መሆኑን በሲቃ ያስረዳሉ።ቦታዉ ለምንም የማይሆን በቆሻሳ የተከበበ መሆኑ የሚገልጹት የሲ.ኤም.ሲ ነዋሪዎች፤ ቤተሰብን ይዞ ጎዳና ላይ ከመሆን ይሻላል በማለት የቀየሱት ጎጆ ያለምንም ርህራሔ መፍረሱ እንዳሳዘናቸዉ ገልጸዋል።
በወረዳዉ እዉቅና ቤት እንደሰሩ የሚናገሩት ነዋሪዎች ቦታዉ ለምንም ነገር መዋል የማይችል ቢሆንም የአቅመ ደካማና የድሃዉ ቦታ ብቻ ተመርጦ የፈረሰ መሆኑ ግራ እንዳጋባቸዉ ይናገራሉ። ለወራት ቤትን በመገንባት ያሳለፉት ነዋሪዎች እንደ አቅማቸዉ በሺዎች የሚቆጠሩ ብሮችን ማፍሰሳቸዉን ያስረዳሉ።
የሚረዳን በሌለበት መልኩ እቃችንን መንገድ ላይ ከምረን ጎረቤት ዘንድ ለግዜዉ ተጠልለናል የሚሉት የሲ.ኤም.ሲ ነዋሪዎች ያለብንን አደጋ ከግምት ዉስጥ በማስገባት የወረዳዉ ባለስልጣናት አስተያየት ያድርጉልን ሲሉም ተማጽነዋል።
በመጪዉ ሮመዳን ያለ መጠለያ ሜዳ ላይ የተጣልን አቅመ ደካሞች በመሆናችን በአገርም ይሁን በዉጭ ያለዉ ወገን እኛንም ልጆቻችንንም ከአደጋ ይታደግ ሲሉ ለቢቢኤን ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment