(ዘ-ሐበሻ) ተማሪዎች በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የመብት ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸማቸውንና ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም በተማሪዎቹ ላይ የሚደርሰው ጉዳት ማየሉ ተዘገበ::
ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ያነሱትን ተማሪዎች ፖሊስ ዛሬ ጠዋት ድረስ መኝታ ክፍላቸው ውስጥ በመግባት እንደቀጠቀጠና ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰ የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች በተለይም አብዛኞቹ ተማሪዎች መፈነካከታቸውና ከ15 የማያንሱ ተማሪዎች በከፍተኛ ጉዳት ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል::
ተማሪዎቹ ከመኝታ ክፍላቸው እንዳይወጡ ህንጻዎች በሙሉ በፌደራል ፖሊሶች እንደተከበበ የሚገልጹት ምንጮች ከሚደርስባቸው ድብደባ ለማምለጥ ሲሞክሩም አንዱን ፌደራል ፖሊስ ከህንፃ ላይ ገፍትረው እንደጣሉትና ፖሊሱም ጉዳት እንደደረሰበት ገልጸዋል::
ፌደራል ፖሊሶቹ በተማሪዎቹ ላይ የሚፈጽሟቸው ግፎች ከድብደባ በላይ አንዳንዱን ተማሪ በጠራራ ጸሀይ ላይ እያንበረከኩ ጸሐይ በማስደብድበ በግሩፕ እንደሚገርፉቸው ያስታወቁት ምንጮቻችን በሴት ተማሪዎች ላይ ሳይቀር ከትናንት ጀምሮ እየተፈጸመ ያለው ድብደባ የሚዘገንን ነው ብለዋል::
በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ውጥረቱ እንዳየለ ሲሆን ዘ-ሐበሻ እየተከታተለች ጉዳዩን ለመዘገብ ትሞክራለች::
ፎቶዎቹን ያሰባሰብናቸው ከሶሻል ሚዲያዎች ነው::
No comments:
Post a Comment