Sunday, May 15, 2016

ቃና የሚባል የቴሌቪዥን ፕሮግራም መላ ካልተበጀለት በቅርብ ቀናቶች ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ እውነታዎች

1) ከፍተኛ የሆነ የትዳር መቃወስ ይፈጠራል
2) ትምህት ቤቶች ይዘጋሉ(የቤት ስራ የሚባል ነገር ይቀራል
3) መስሪያ ቤቶች የስራ ሳይሆን የእንቅልፍ ቦታ ይሆናሉ
4) የሚወለዱ ህፃናት በሙሉ ዘሀራ ወይም ቻንድራ የሚል ስም ይወጣላቸዋል
5)EBC # ebc ውስጤ ነው# በሚል logo ይቀይራል
6) አውቶብሶች በሙሉ ዲሽ ያስፈልገናል በሚል አድማ ይመታሉ
7) መንገዶች በሙሉ ቃና ቃና በሚል እግረኞች ይጨናነቃሉ
8) ፍቅረኛሞች እወድሻለው የሚል ቃል ቀርቶ ውስጤ ነህ በሚል ቃል ይተካል ይመ አስተናጋጆች ሜኑ ሲጠየቁ ቃናም አለ ይላሉ
10) የካፌ፡የሆቴል የምግብ ዋጋ በ3እጥፍ ይጨምራል
11) ሳያዙ ሳይሆን ” እነ እንትናን ሊያዪ መቀመጥ ክልክል ነው “በሚል ማስጠንቀቂያ ሬስቶራቶች ይጨናነቃሉ
……
12) የሰዓት መለኪያችን ቃና ላይ በሚታዩት ፊልሞች ይሆናል ማለትም “ፍሬንዴ ሰዓት ሲባል ባክ ገና ነው ጥቁር ፍቅር
አልጀመረም” መባባላችን የማይቀር ነው
13) የፌስ ቡክ ፕሮፋይል ፒክቸሮች በነቻንድራ,በነ ኦማር,በነ ጁሊያ.. … ምስል ይቀየራል
14) በአንፃሩም የፌስ ቡክ የፕሮፍይል ስሞች በቃና ፊልሞች ስሞች ይቀየራሉ በአብዛኛው የሴቶች ስም ለምሳሌ;አበሩ ኦማር ጋል፣ኪዱ
ጁሊያን ወጥመድ…..ሌላው ደግሞ ከበፊቶቹ የተበረዙስሞች ጋር ..ቻንድራ ብሪዚ ብራውን…. በሚል መቀየራቸው የማይቀር ነው
።።።።።።።።።።።።፡፡።።።
“ባጠቃላይ ሀገሪቷ እንቅልፋም፡የደነዘዘ፡…… ዜጋን ማምረት ትጀምራለች”
by Endris Muktar

No comments:

Post a Comment