ከጋምቤላ የታፈኑትን ሕጻናት ለማስለቀቅ በለጋሾች ትብብር በአንድ ሕጻን $5000 ዶላር ተከፍሏል:: #Ethiopia #Gambella#SouthSudan #EPRDF #MinilikSalsawi #Freedom
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – መናገር ሳንፈልግ የምታናግሩን እንደምን አደራችሁ::ይህ ባለፈው በጋምቤላ ክልል የተደረገውን ወረራ እና አፈና ጋር የተያያዘ መረጃ ነው:: ከበባ ላይ ነን ቢሉም ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቆ የገባ የሕወሓት ሰራዊት እንዳሌለ እና የታፈኑ ሕጻናትን ለማስለቀቅ በደቡብ ሱዳን መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ሹሞች የተመራ ድርድር እንደነበር ተጠቅሶ በዚ ገጽ ላይ ተጽፎ የነበረ ቢሆንም መረጃውን ለመቀበል አሻፈረኝ ሲሉ የነበሩ ሁሉ ዛሬ ላይ የሕጻናቱን በድርድር መለቀቅ ተከትሎ ሲያሞጠሙጡ እያየን ነው::
በጋምቤላ ክልል ዘልቀው ገብተው መንግስት ያሌላትን አገር ድንበር በመገርሰስ ከመቶ በላይ ሕጻናትን አፍነው የወሰዱት የሙርሌ ታጣቂዎች በደቡብ ሱዳን SPLM የጦር አበጋዞች እየተደገፉ በኢትዮጵያውያን ላይ ወረራ ፈጽመዋል::ይህን ለማስቆም ባለመቻሉ በቂ የመከላከያ ታማኝ ሃይል በሃገሪቱ ባለመኖሩ ግድያ ዘረፋ እና አፈና ተፈጽሟል::ይህን ግድያ እና አፈና ዘረፋ ተከትሎ ሕወሓት መራሹ አገዛዝ ታጣቂዎችን ከብቤአለሁ ቢልም በአከባቢው ያሉ ታማኝ ምንጮች ግን የአገዛዙ ወታደሮች በፍጹም ድንበር ተሻግረው እንዳልሄዱ ተናግረዋል::( https://www.facebook.com/photo.php?fbid=1713785818892614&set=pb.100007836377373.-2207520000.1462968302.&type=3&theater ) አዲስ አበባ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶችን የሕወሓት አገዛዝ ከሙርሌ ታጣቂዎች ጋር እየተደራደረ እንደኖነ በጊዜው አሳብቀዋል::(https://www.facebook.com/photo.php?fbid=1715679065369956&set=pb.100007836377373.-2207520000.1462968302.&type=3&theater )
በድርድሩ መሰረትም ሕጻናቱን ለማስለቀቅ በለጋሾች ትብብር አንድ መቶ ሺህ ዶላር ለሃያ ሕጻናት የተከፈለ ሲሆን የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ከተረከቡት ሃያ ሕጻናት ውስጥ አንዱ ባልታወቀ ምክንያት በመሞቱ አስራዘጠኝ ሕጻናትን ለሕወሓት ወታደራዊ ቅልብ ወታደሮች ማስረከባቸውን የደቡብ ሱዳን የአዲስ አበባ ዲፕሎማቶች ይናገራሉ::የሕወሓት ሰራዊት በድንበር አከባቢ በሂሊኮፕተር መጥቶ እንደተረከባቸው የሚናገሩት ዲፕሎማቶቹ ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቆ የገባ ምንም የውጪ ሃይል የለም ሲሉ አስረግጠው ገልጸዋል:: ሕጻናቱን ለማስለቀቅ በተደረገው ድርድር ላይ የምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ አታሼዎች እና ሁለት የዩኒሴፍ የሰላም አምባሳደሮች ተሳትፈዋል::ድርድሩ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ቀሪ ሕጻናትን ለማስለቀቅ ተመጣጣኝ ገንዘብ ቱርክ ኳታር እና ጀርመን እንዲሰጡት ወያኔ ተማጽኖ አቅርቧል::#ምንሊክሳልሳዊ
No comments:
Post a Comment