ወደ ባይ ዶዋ አካባቢ የተሰማሩ የአሸባብ ታጣቂዎች ሶስት የኢትዮጵያን ወታደሮች አግተዉ የአል_ሸባብ ወታደራዊ ጣቢያ (base ) ወደ ሆነው ኢልቡር (El_bur ) መውሰዳቸዉን የሚጠቁሙ መረጃዎች ሕወሓት ለሚመራው የምስራቅ እዝ ወታደራዊ ደህንነት እንደደረሱት ተገለጸ::
እንደዘገባው ከሆነ በቅኝት ላይ ተሰማርተዉ ከነበሩ ጥቂት የዝውዉር ወታደሮች መካከል ሶስቱ መሰወራቸዉን ተንተርሶ ፍለጋ ቢደረግም ምንም አይነት ፍንጭ ጠፍቶ የነበረ ሲሆን ወታደሮቹ በአል_ሸባብ መጠለፋቸዉን የሚጠቁሙ መረጃዎች ከወደ ኢልቡር መንደር እንደደረሰዉ የስምሪት አዛዡን ተንተርሶ አንድ የምክትል መቶ አለቃና ሌሎች ተራ ወታደሮች መጠለፋቸዉን በሶማሌያ የኢትዮጵያዉ ጦር አዛዥ ኮረኔል የማነገብረ ማርያም ለምስራቅ እዙ ማሳወቃቸውም ተሰምቷል::
በታህሳስ ወር 2006 እ.ኤ.አ የተመሰረተዉ “አልሸባብን ማጥፋት ማለት መላዉ የሶማሌያን ሕዝብ ማጥፋት ማለት ነዉ የሚል አባባል አለ” የሚሉት የዚህ ዜና ምንጭ አልሸባብ ማለት እጅግ ጨካኝና አረመኔ የጥፋት ቡድን ነዉ ብለዋል:: ከአልሸባብ ጋር የሚደረጉ ትንቅንቆች በሙሉ ከሶማሌያ ህዝብ ጋር የሚደረግ ትንቅንቆች ናቸው እስኪባል ድረስ ምንም እንኳን በዚህ በሶማሌያ ያሉት የኢትዮጵያ ወታደሮች መጠን ቢቀነስም የአልሸባብ ድንገተኛ ጥቃት ግን ፈጽሞ አልቀነሰም:: አሁን የተጠለፉት ወታደሮቻን የሚጠብቃቸዉ የከፋ ሞት ብቻ ሊሆን እንደሚችል የዜና ምንጩ ለዚህ ዜና ዘጋቢ ገልጸዋል:
No comments:
Post a Comment