Friday, May 13, 2016

ወታደራዊ መኮንኖች ራሳቸውን በተሳሰረ ኔትወርክ በተለያየ የማፊያ ቡድን ማደራጀታቸው ለኢትዮጵያ ከባድ ስጋት ተደቅኖባታል::

ሃገራችን አደጋ ላይ ናት – ለማዳን እንረባረብ!!! በአገር አንድነት ሽፋን ደም መጣጮቹ የደርግ መኮንኖች በሃገር እና ሕዝብ ላይ የሰሩት አሳፋሪ በደል ቁስል ሳይደርቅ በብሄር ብሄረሰቦች መብት ሽፋን ሰው በላዎቹ የሕወሓት ወታደራዊ መኮንኖች በተሳሰረ ኔትወርክ የተለያዩ የማፊያ ቡድኖችን በማደራጀት የቢዝነስ ኢምፓየርነታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ የሚወስዱት እርምጃ አገሪቷን አደጋ ውስጥ የከተቷት መሆኑን እና ከባድ ስጋት በሃገር እና ሕዝብ ላይ መደቀኑን ከቡድኑ አባላት የሆኑ ምንጮች የተገኘ መረጃ ጠቁሟል::
የመከላከያ ሰራዊት ብሎ ራሱን የሚጠራው የታጠቀ ሰራዊት በሚመለከት ከተሰበሰቡ መረጃዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የወታደራዊ መኮንኖች በራሳቸው ኔትወርክ ያደራጁት አደገኛ ቡድን ካለው የሕወሓት አገዛዝ ላይ ስልጣን እስከመረከብ እና ወንጀለኛ እና ሌባ ባለስልጣናትን እስከማሸሽ ድረስ እቅድ ይዞ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በሃገሪቱ ላይ የሚደረጉ የፖለቲካ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር ላይ ሲገኝ ከሕግ በላይ የማሰር የመግደል የመዝረፍ የመፍታት የማሳደድ ስልጣን ለራሱ ሰጥቶ በስፋት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ የጠቆሙ ሲሆን ለቡድኑ አባላት ለሆኑ ወታደሮች ከፍተኛ ገንዘብ የሚከፈል ሲሆን በዛ ያሉ ጥቅማ ጥቅሞችን እንደሚደርግ ተናግረዋል::
በደህንነት ተቋም ውስጥ እንዲሁ ከፍተኛ ዘረፈ እስር ግድያ እና አፈና የሚፈጽሙ ከመንግስት እና ሕግ በላይ የሆኑ ቡድኖች እንዳሉ ከዚህ ቀደም መጠቀሱ አይዘነጋም::የሃገሪቱን አንጡረ ሃገር ለሃገሪቱ መጥፊያ እያዘጋጁ መሆኑን እያንዳንዱ ዜጋ አውቆ እነዚህን የማፊያ ቡድኖች በመታገል ከሃገራችን ምድር ላይ ለማስወገድ ሌትተቀን ልንሰራ የምንገደድበት ጊዜ ላይ መሆናችንን ማወቅ አለብን:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.

No comments:

Post a Comment