Tuesday, May 10, 2016

ኬንያ ለሃገሪቱ ፀጥታና መረጋጋት የስደተኞች መጠለያ ሠፈሮችን ለመዝጋት መወሰኑን አስታወቀ።

የኬንያ መንግሥት በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ሠፈሮችን ለመዝጋት መወሰኑን አስታወቀ
ከሃገሪቱ የሃገር ግዛት ሚኒስቴር ከትናንት በስተያ፤ ዓርብ የወጣ መግለጫ እንዳመለክተው የኬንያ መንግሥት ለሃገሪቱ ፀጥታና መረጋጋት ሲል ይህንን እርምጃ ለመውሰድ መገደዱን አስታውቋዋል።
መግለጫው የኬንያ የስደተኞች ቢሮ መዘጋቱን ያስታወቀ ሲሆን አንድ የቢሮው ባልደረባ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል ግን ጉዳዩ ሰፊ ማብራሪያ ስላልተሰጠበት በሃገሪቱ ውስጥ ያሉ ስደተኞች የእርምጃው ሁኔታ በግልፅ እስኪታወቅ በርጋታ እንዲቀመጡ ማሳሰባቸውን ናይሮቢ የሚገኘው ሪፖርተራችን ገልሞ ዳዊት ዘግቧል፡፡
የኬንያ የሃገር ግዛት ሚኒስቴር ትላንት ባወጣው መግለጫው በተለይ የአልሻባብንና የሌሎች የሽብር ቡድኖችን ጥቃት ለመከላከል ሲል ሃገሪቱ ስደተኞችን ማስተናገድ ለማቆምና መንግሥቷም እዚያ ያሉ ስደተኞችን ለመመለስ መወሰኑን አስታውቋል።
መግለጫው አክሎም ዳዳብ ና ካኩማ የሚባሉት ሁለቱ ግዙፍ የስደተኞች መጠለያ ሠፈሮች ከ30 ዓመታት በላይ ያሉ በመሆናቸው የሚኖሩባቸው ስደተኞች ለሃገሪቱ ሸክም ሆነዋል ብሏል።
“ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም ለስደተኞቹ ቋሚ መፍትሄ አልሰጠም” ሲልም መሥርያ ቤቱ ቅሬታውን ገልጿል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር – ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር. የኬንያ ቅርንጫፍ በበኩሉ መግለጫው ለድርጅቱም አዲስ በመሆኑ ስለሁኔታው በመጭው ሣምንት ውስጥ ከኬንያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያይ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።
ኬንያ ከሚገኙት ስደተኞች የሚበዙት ሶማ

No comments:

Post a Comment