የሀገራችን የአፈፃፀም ችግር የጥንት የጠዋት ነው፡፡ ህግጋት ይደነገጋሉ፡፡ መመሪያዎች ይወጣሉ፡፡ ማዘዝ ቁልቁለት ነውና ትዕዛዛት ይፈስሳሉ፡፡ ግን በተግባር ሥራ ላይ ውለው አይገኙም፡፡ በየእርከኑ ያሉ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት፤ ወይ ነገሩን ከጉዳይ አይጥፉትም፤ ወይ በግላቸው እንዳይፈፀም ይሻሉ፤ አሊያም ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ምክንያቶች እየደረደሩ ባለጉዳይ ማጉላላታቸውን ይያያዙታል፡፡
ስብሰባዎች የኑሮ ዘዴ እስኪመስሉ ድረስ በተደጋጋሚ “ስብሰባ ላይ ናቸው”ን መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡ ከአንድ ቢሮ ወደ ሌላ ቢሮ ጉዳይ የያዘ ፋይል ሲንፏቀቅ ይከርማል፡፡ ዳር የደረሰው ፋይል ደግሞ “ይሄ ይሄ አልተሟላም” ተብሎ ጉዳዩ መልሶ ጥሬ ይሆናል፡፡ የደከመው ባለጉዳይ እርም ብሎ ከነጭርሱ ነገሩን ይተወዋል፡፡ ያልታከተው ባለጉዳይ ሥራ ያቀላጥፍልኛል ወዳለው ሹም በአማላጅ ለመሄድ ይጥራል፡፡ ይሄ የባለጉዳይ መጉላላት እጅግ ሲደጋገም “ጉዳይ አስፈፃሚ” የሚል ታርጋ ያለው፤ በውል በ “ቢ ፒ አር” የማይታወቅ ማዕረግ ያነገበ፣ ሠራተኛ ፈጥሮ ቁጭ ይላል፡፡ ዛሬ በማናቸውም መሥሪያ ቤት ያለ ሥራ፣ ከተቋሙ ውጪ በሚኖር “ጉዳይ አስፈፃሚ” የሚተዳደር ይመስላል፡፡ የቢሮክራሲውን ቀይ ጥብጣብ (bureaucratic red tape) የሚበጥሱ ጉዳይ አስፈፃሚዎች” ናቸው፡፡ “ከእያንዳንዱ አሸናፊ ወንድ ጀርባ አንድ ሴት አለች” ይባል የነበረው፤ በዛሬው የአገራችን ሁኔታ፤ “ከእያንዳንዱ ስኬት ጀርባ አንድ ጉዳይ አስፈፃሚ አለ” የሚባልበት ወቅት ተፈጥሯል፡፡ አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት፤ በስሪያ ቤት ውስጥ ያሉ ሠራተኞች እርስ በርስ ሥራውን ለማሳካት “ጉዳይ አስፈፃሚ” ይፈልጋሉ ተብሏል፡፡
“ገንዘብ የደም ሥር ነው” የሚለው የጥንት አባባል፣ ዛሬ ዐይን ባወጣ መልኩ እንደ ዱላ ቅብብል ሥራ ማስኬጃ መሆኑ የአደባባይ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነወ፡፡
ከአንድ ቢሮ ጉዳይ ለማንቀሳቀስ ህጉ፣ ባለጉዳዩ የያዘው ገንዘብ ነው፡፡ ፀሐፊዋ ያለገንዘብ፣ ፋይል ለአለቃ አታቀርብም፡፡ በአንዳንድ አጋጣሚ በፈገግታ “ጉዳይህ ምንድነው” ለማለት ገንዘብ ትሻለች፡፡ አለቃዋ፤ አሉ የሉም፤ ለማለትም ገንዘብ ያስፈልጋታል፡፡ ጉዳይ ከተፈፀመ በኋላም ገንዘብ እንደማህተም የሚያገለግል የፋይሉ አካል ነው፡፡ ይሄን እንደምሳሌ ጠቀስን እንጂ ከተላላኪ እስከ ሥራ አስኪያጅ፣ ከዚያም እስከ ቦርድ ሰብሳቢ ድረስ፤ መላው ይሄ ሆኗል፡፡ እንግዲህ ይሄ አካሄድ “እየተሻሻለ መጥቷል” በተባለው የመልካም አስተዳደር ዘይቤ ውስጥ ያለ ነው፡፡ “ፍትሐዊ አሠራር እየሰፈነ ነው” በሚባልበት አገር ነው፡፡ “እጅህን እኩሬው ውስጥ ክተት፡፡ ወይ አሣ ታገኛለህ፤ ካልሆነም እጅህን ታጥበህ ትወጣለህ” ነው የትም ቦታ ያለው ሙስናዊ መርህ፡፡ አንዳንድ ሰፈር፤ “አለዛ (ያለገንዘብ) እንዴት ሥራ ይሠራል?” የሚለው አነጋገር የመጽሐፍ ቃል ይመስላል፡፡
አንድ ፀሐፊ እንዳለው፤ “የአፍሪቃ አማፂያን ድል ባደረጉ ማግስት ገንዘብ ማርባት ይጀምራሉ፡፡ ከዚያም ራሳቸው ይሰባሉ፡፡ በመጨረሻም ዕውነተኛው ግብ ራስን ማድለብ ይሆናል”፡፡ (At the end, the real goal becomes fattening oneself) ስለፈጣን ልማት እያወራን ፈጣን ስባት ውስጥ ከገባን፣ ልማቱን ወደ ፈጣን ጥፋት ለወጥነው ማለት ነው፡፡ በቪላዎች፣ በፎቆች፣ በመሬት ብዛት፣ በባንክ ደብተሮች ቁጥር ብዛት፣ በልጅ በዘመድ አዝማድ ውክልና ብዛት ወዘተ… በአጠቃላይ በግል ልማት፤ የአገርን ልማት ተክተን የምንንቀሳቀስ ከሆነ፤ ወሰን-የለሽ መንኮታኮት ገና ይጠብቀናል፡፡ እስር ቤቶች ያለጥርጥር ሞልተው ይትረፈረፋሉ፡፡ የሚገርመው፤ የሚሞሉት በጉቦ ተቀባይ ብቻ ሳይሆን በጉቦ-ሰጪም ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ፤ ጉቦ-ተቀባዩ በምን መልክ መቀበል እንዳለበት ተጨንቆ ተጠቦ መላ የሚዘይድለት ራሱ ጉቦ-ሰጪው የሆነበት ደረጃ በመድረሱ ወደ ባህልነት ተሸጋግሯ፡፡ ጉዳይ አስፈፃሚው እንደ ህግ አማካሪ ማገልገሉም አይገርምም – የልምድ አዋላጅነት ፈጣን ገቢ የማከማቻ አቋራጭ ሆኗልና!

በአቋራጭም ሆነ በረዥሙ መንገድ መንጋ በላተኛ ፈጥረናል፡፡ ደላሎቹ እንደሚሉት፤ “የሥራው ፀባይ ነው” ማለት በሙስናም ረገድ የማያሳፍር አባባል ነው፡፡ ትላልቅ ውሸቶች የጥቃቅንና አነስተኛ ውሸቶች መድብል ናቸው፡፡ አያሳፍሩም፡፡ ገንዘብህን የበላ፣ መሬትህን የበላ፣ ንብረትህን የበላ፤ አንተን ከመብላት ወደ ኋላ አይልም – “መብላት የለመደ ሲያይህ ያዛጋል” የሚባለው ለዚህ ነው!!
Source Addis Admass
No comments:
Post a Comment