የአርበኞች ግንቦት 7 የዜና ምንጮች እንደገለጹት ፕሮፌሰሩ በአሜሪካ ቆይታ ካደረጉ በኋላ ወደ አውሮፓ ጁን ላይ ጉዞ ያደርጋሉ::
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደም ከአስመራ ወደ አሜሪካ በመጡበት ወቅት “ትግላችን ያለው ሃገር ቤት ነው” ያሉ ሲሆን ትላንት ለኢሳት ራድዮ በሰጡት መግለጫ “ቃላችንን እያከበርን ነው… በአርባምንጭ እንደወሰድነው እርምጃ በተለያዩ ቦታዎች እርምጃዎችን እንወስዳለን” ብለዋል::
አርበኞች ግንቦት 7 በመንግስት ወታደሮች ላይ እንዲህ ያለውን ጥቃት በአርባምንጭ ከወሰደ በኋላ የሥርዓቱ ደጋፊ የሆኑ ግለሰቦች ካሁን በኋላ “ፕሮፌሰሩ አሜሪካ አይመጡም; አሜሪካ እንዲህ ያለውን የግንቦት 7 ድርጊት አትደግፍም”እያሉ አስተያየት ሲሰጡ ቢቆዩም ፕሮፈሰሩ ግን ለሥራ ጉዳይ እዚህ ገብተዋል
No comments:
Post a Comment