ሐሰተኛ ስም በመጠቀም የቀበሌ መታወቂያ በማውጣትና ሐሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሜን
አዲስ አበባ ዲስትሪክት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ቅርንጫፍ 27,876,705 ብር በማጭበርበር የተጠረጠሩ
የባንኩ ሠራተኞችና ግለሰቦች መታሰራቸው ታወቀ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ወክላ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተባለ ድርጅት የተመሠረተ በማስመሰል ሐሰተኛ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የመመሥረቻ ጽሑፍና የመተዳደሪያ ደንብ በማቅረብ በድርጅቱ ስም አዲስ ሒሳብ መክፈታቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ አዲስ እንዳቋቋሙት በተገለጸው ወክላ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ስም በከፈቱት የሒሳብ ቁጥር 10001521550078 ውስጥ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኛ ከሆኑ የተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በድምሩ ከላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን በማውጣት ማስገባታቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሒሳብ ላይ በማውጣት ወደ ድርጅታቸው ያስገቡትን ገንዘብ በተለያዩ ግለሰቦች ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በዳሸን ባንክ፣ በወጋገን ባንክ፣ በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክና በሁሉም የመንግሥትና የግል ንግድ ባንኮች ሒሳብ በመክፈት ገንዘቡን ቀናንሰው ማስቀመጣቸውም ተጠቁሟል፡፡
የተወሰኑት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት በመቅረብ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የተጠየቀባቸው ሲሆን፣ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ፖሊስ በክትትል ላይ መሆኑም ታውቋል፡፡ ባንኩ የጠረጠራቸውን ሠራተኞች ስም ዝርዝር በመጥቀስ እንዲከታተልለት ለፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ያመለከተ ቢሆንም፣ ኮሚሽኑ የክትትሉንና የምርመራ ሥራውን ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ማስተላለፉ ታውቋል፡፡
የፌዴራል የወንጀል ምርመራ ዘርፍ የተወሰኑትን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመረ መሆኑን፣ የ11 ተጠርጣሪዎችን የባንክ ሒሳብ (በሁሉም የንግድ ባንኮች) እንዲታገድ ማድረጉን የሪፖርተር ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

Leave a Reply