Friday, May 6, 2016

የሰሜን ሱዳን ወታደሮች በተራቸው ኢትዮጵያን ጥሰው ገብተው እያፈኑ መውሰድ ጀምረዋል” ቪኦኤ May 6, 2016 – ቆንጅት ስጦታው — Comments ↓


“የሰሜን ሱዳን ወታደሮች በተራቸው ኢትዮጵያን ጥሰው ገብተው እያፈኑ መውሰድ ጀምረዋል” ቪኦኤ
++++++++++++++++
ከጥቂት ወራት በፊት : የ ኤርትራ ወታደሮች ወርቅ ለማውጣት ይቆፍሩ የነበሩ በርካታ ወጣቶችን ታፍነው መወሰዳቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ገልጾ ነበር:: ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደግሞ ዩኒፎርም የለበሱ የደቡብ ሱዳን ወታደሮች ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን ገድለው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕጻናትን አፍሰው መውሰዳቸውን አሁንም የኢትዮጵያ መንግስት ገልጿል:: አሁን ደግሞ የሰሜን ሱዳን ወታደሮች ቤንሻንጉል ድረስ ገብተው በርካታ ኢትዮጵያውያንን አፍነው ወስደው ሱዳን እንዳሰሯቸው እና ሌሎቹም የት እንደገቡ እንደማይታወቅ ባለሀብቶች እየገለጹ ነው::
ቀጥሎስ ተረኛው ማን ይሆን? የጅቡቲ ወይስ የኬንያ ወታደሮች?
አልኑር በሽር ሲባል በቆየ በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል በጉባ ወረዳ በኦሜድላ ቀበሌ ባለ እርሻ ልማት ላይ የሚሠሩ 22 ሠራተኞች በሱዳን ወታደሮች ተጠልፈው መወሰዳቸውን የእርሻ ልማቱ ባለቤት ነኝ ያሉት አቶ ይርሳው የሺወንድም ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment