Monday, May 2, 2016

ኢቢሲ/ኢቲቪ ፋሲካን በጂንካ // ፡ ‹‹ላም ባልዋለበት –ቁበት ለቀማ›› Girma Bekele


ኢቢሲ/ኢቲቪ ፋሲካን በጂንካ // ፡ ‹‹ላም ባልዋለበት –ቁበት ለቀማ›› Girma Bekele
የደቡብ ቴሌቪዥን ሰፊ የአየር ጊዜ ሰጥቶ ‹‹ፋሲካን በቴሌቪዥን›› እያስኮመኮመን በቲቪ ቁንጣን ስንሰቃይ አሳልፈናል፡፡
እኛና ህዝብ በክልላችን ታሪክ አይተን በማናውቀው ፈተና ውስጥ ነን እያልን ነው፡፡ በዓሉም ቢሆን ያለፈው ቅቤ በለመድንበት ዘይት አሮብን ነው ብለን አስቀድመን ተናግረናል፡፡ የህወኃትን የ11 ከመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት በቴሌቪዥን ከማየት የዘለለ ትርጉም አጣንበት፣ የኑሮው ውድነት ከሸክማችን በላይ ሆነ እያልን ባለንበት ፣… የኢቢሲ የቴሌቪዥን ድግስ ‹ በሰው ቁስል እንጨት ከመስደድ ›የተለየ ትርጉም አይኖረውም፡፡ ግና የሚናገርበት አፍ እንጂ የሚሰማበት ጆሮ የሌለው የህወኃት/ኢህአዴግ ቡድን ዛሬም እንደለመደው የፋሲካን በዓል በዞናችን ዋና ከተማ በማክበር በቤታችን ያላየነውን በዓል በቴሌቪዥን እያሳየን በሃሳባችን በቁንጣን እየተሰቃየን እንድናሳልፍ አድርጓል፡፡ ይህ የሚያሳየው የህወኃት ዘረኛ ቡድን ‹‹ያደቆነ ሠይጣን ሳያቀስስ አይለቅም›› ውስጥ መገኘቱን እንጂ የእኛን ኑሮ አያይደለም፡፡ በብሄር ብሄረሰቦች ቀን ራቁታችንን መጨፈራችን እነሱን ከማዝናናት ያለፈ ትርጉም እንደሌለው ሁሉ የፋሲካ በዓል በጂንካ መከበር ለእኛ ሌላው ቀርቶ ለበዓሉ ዘይት አልሆነንም ፡፡
ትግላችን በእኩልነት ላይ ለተመሰረተ አንድነት፣ ለፍትሃዊ ዕድገት ስርጭትና ተጠቃሚነት፣ የህግ የበላይነትና የአገር ሉዓላዊነት መከበር ፣ የዜጎች ክብር መመለስ…. በመሆኑ በአንድ ቀን የቴሌቪዥን ሆይ-ሆይታ አቅጣጫውን አይስትም፣ አይዘወርም፡፡ ይልቁን የሃመር ወጣቶችን የፍትህ ጥያቄ መልሱ፣ በኢንቨስትመንት ስም የሚታካሂዱትን ዘረፋ አቁሙ፣ በስኳር ልማት ስም ለሚፈጸመው ሙስና ገደብ አኑሩለት፣ ለህዝቡ የመልካም አስተዳደር፣ የልማትና የኑሮ ውድነት ጥያቄ መልስ አዘጋጁ፣ መፈናቀልና የተፈጥሮ ሚዛን ማናጋት ያብቃ፣የንግድ ድርጅታችሁን ወንዶ ኩባንያ እጅ ከህዝቡ ላይ አንሱለት፣በህዝብ ላይ በሽብር ስም በጠብመንጃ የሚታካሂዱትን አፈና አንሱለት፣የካሮ ህዝብ ‹በረሃብ ልናልቅ ነውና ድረሱልን› ያለውን አድምጡት…. የህዝብን የሰብዐዊ መብትና የዲሞክራሲ ጥያቄ በህገመንግስቱ መሰረት አክብሩለት፡፡
እነዚህ ባልተመለሱበት በብሄራዊ ዕርቅና መግባባት በሚመሰረት የሽግግር መንግስት አዲስቱን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እስከምንገነባ በምንም መልኩ ፕሮፖጋንዳችሁ ከነጻነት ትግላችን አያዘናጋንም፡፡ ‹‹እኛም አውቀናል ፣ጉድጓድ ምሰናል›› እንዲሉ የፕሮፖጋንዳ ሰለባ ላለመሆን ቀድመን ነቅተናልና ‹‹ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ›› በከንቱ አትንከራተቱ ፡፡ ነገረ ስራችሁ ሁሉ ‹‹ሆድን በጎመን ቢደልሉት ….. ›› መሆኑን ለመረዳት ስንት ዓመት ይፈጅባችኋል ወይስ ለሴራችሁን ተንኮላችሁ ከላይ የወረደባችሁ ፍርድ ነው ?
ኢቲቪ/ኢቢሲ ሆይ ‹‹–ተነቃቅተናልና በተበላ ደረቅ ፕሮፖጋንዳ ሲባል እናንተና መሰሎቻችሁ ተሰባስባችሁ በመጨፈርና በማስጨፈር
በከንቱ አታባክኑት፡፡
በተመሳሳይ በቀጣይ ወር መጨረሻ ሌላ የልማት ገቢ ማሰባሰቢያ ባዛር መታቀዱንና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን እናውቃለን፡፡ የተወደዳችሁ የህዝብ ተወካይ ‹ነጻ › የልማት ባዛር አዘጋጆች እባካችሁ ህወኃት/ ኢህአዴግ ከፊቱ የተደቀኑትን የተለያዩ የህዝብ ጥያቄዎች ለማስቀየስ በሚያካሂደው ደረቅ ፕሮፖጋንዳ የሚባክነውን የአገርና ህዝብ ሃብት በቅርብ እየጮሁ ያሉትን በረሃብ የተጎዱ ‹የካራ ህዝብ› ይታደግበት ዘንድ ምከሩት እንጂ አውቃችሁም ሆነ ሳታውቁ የፕሮፖጋንዳው ግብረሃል አትሁኑ ፡፡ ›› ምክራችን ነው፡፡
በቸር ያገናኘን ፡፡ 24/08/08. UNITE.



Leave a Reply

Your email address will not be published.

9 + 4 =

No comments:

Post a Comment