(ዘ-ሐበሻ) ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ቤት ከቆዩ በኋላ አብረሃ ደስታ፡ የሺዋስ አሰፋ፡ ሀብታሙ አያሌው፡ ዳንኤል ሺበሺና አብረሃም ሰለሞን በነጻ እንዲሰናበቱ ፍርድ ቤት ባለፈው ኦገስት 2015 ቢወስንም ችሎት ደፍራችኋል ተብለው የእስር ቅጣት የተጣለባቸው አብረሃ ደስታ; የሺዋስ አሰፋና ዳንንኤል ሺበሺ እስር ቤት እንዲቆዩ መደረጉ አይዘነጋም::
በዚህም መሰረት የ እስር ጊዜያቸውን የጨረሱት የቀድሞዎቹ የአንድነትና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የሺዋስ አሰፋና ዳን ኤል ሺበሺ ዛሬ ከ እስር መፈታታቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ከነዚሁ ታዋቂ ፖለቲከኞች ጋር ታስሮ የሚገኘው አብርሃ ደስታ እስካሁን በ እስር ላይ ይገኛል:: አብርሃ ደስታ የተጣለበትን ቅጣት የሚጨርሰው የሚቀጥለው ሰኔ ወር ላይ ነው::
No comments:
Post a Comment