Tuesday, May 10, 2016

ውይይት ከሻለቃ ዳዊት ወልደ-ጊዮርጊስ ጋር

ውይይት ከሻለቃ ዳዊት ወልደ-ጊዮርጊስ ጋር


ሻለቃ ዳዊት ወልደ-ጊዮርጊስ ከቪኦኤው ስትሬት ቶክ አፍሪካ ጋር ቃለ-ምልልስ እያደረጉ እ.አ.አ. 2013
ሻለቃ ዳዊት ወልደ-ጊዮርጊስ Major Dawit WeldeGiorgis Interview
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅ መከሰቱ፣ በዚህም ሚክንያት አያሌ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለራብ መጋለጣቸው፣ ሕይወታቸውን ያጡም እንዳሉ፣ ድርቁም አስጊና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የዓደባባይ ምስጢር ነው።
የዛሬ እንግዳችን ሻለቃ ዳዊት ወልደ-ጊዮርጊስ ናቸው። የውትድርናውን መጠሪያ ያገኙት ሐረር ጦር አካዳሚ ገብተው እስከ መቶ እልቅና እንደዘለቁ፣ ከዚያም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ህግ ከተማሩ በኋላ ሻለቃ እንደተባሉ አጫውተውናል። ይህ ነው የመለያ ማእረጋቸው ታሪክ።
የዛሬው ወጋችን ግን በሕይወት ታሪካቸው ማለትም ስለ አስተዳደጋቸው ወይም ስለ ትምህርት ቤት ሕይወታቸው ሳይሆን፣ (ያ ለሌላ ጊዜ ይቆየንና) ዛሬ የምናተኩረው ይበልጥ በሚታወቁበት በእርዳታ ማሰባበሪያና ማቋቋሚያ ኰሚሽን አገልግሎታቸው ዙሪያ ይሆናል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅ መከሰቱ፣ በዚህም ሚክንያት አያሌ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለራብ መጋለጣቸው፣ ሕይወታቸውን ያጡም እንዳሉ፣ ድርቁም አስጊና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የዓደባባይ ምስጢር ነው።
በመሆኑም በዚህ አሳሳቢ ጉዳይ፣ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ እንግዶችን፣ ባለሙያዎችን እየጋበዝን አወያይተናል። ሻለቃ ዳዊትም ለዚህ ዓይነቱ ርዕስ ተገቢ እንደሚሆኑ በማመን፣ ከእርሳቸው ጋር ካደረግንው ሰፊ ውይይት፣ ለዛሬ በወቅታዊው ድርቅና ረሀብ፣ እንዲሁም በመፍትሔ ሃሳቡ ላይ ብቻ እናተኩራለን። ያወያያቸው አዲሱ አበበ ነው።

No comments:

Post a Comment