Tuesday, May 10, 2016

በብኣዴንና በኦሕዴድ ካድሬዎች ላይ የሕወሓት የበላይነት በስልጠና ሽፋን የሚቀጥለው እስከመቼ ነው?


በብኣዴንና በኦሕዴድ ካድሬዎች ላይ የሕወሓት የበላይነት በስልጠና ሽፋን የሚቀጥለው እስከመቼ ነው?
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎ANDM‬ ‪#‎OPDO‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Change‬
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ጸሃይ የሚሞቅ ውሻ ሁሉ ሞኝ የሚመስላቸው ሕወሓቶች ካለፉት ሳምንታት ጀምረው ለሶስት ወራት የሚቆይ የኢህአዲግ ከፍተኛና መካከለኛ የአመራሮች ስልጣናን ግምገማ በመቀሌ አስጀምረው የሕወሓትን የበላይነት በሃይል ለመጫን እና ለማሳመን ካድሬዉም ሄዶ ሕዝቡን እንዲያሳምን ለማድረግ በስልጣና ሽፋን እየተውተረተሩ ይገኛሉ::ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከኦሕድድ የተወጣቱ ካድሬዎች በተወሰኑ የብኣዴን እና ሕወሓት ካድሬዎች ታጅበው ስልጠና እና ግምገማ ላይ ሲሆኑ ዋናው አላማ በኦሮሞ ክልል የተነሳውን ሕዝብዊ እንቅስቃሴ ዳግም እንዳይከሰት ታዛዥ እና ሕዝብን የሚያኮላሹ ካድሬዎችን በመፍጠር ለሕወሓት ተገዢ የሆነ ትውልድ ማፍራት ነው::
ኦሕደዽ እና ብአዴን አለቃቸው ሕወሓት ያዘዘውን በመፈጸም የሚረኩ ጥርቅሞች ናቸው።ከተለያዩ ክልሎች ተወጣጥተው የሚሰለጥኑ ካድሬዎች ቢኖሩም አንደኛው ቡድን በባህር ዳር በግምገማ እና ስልጣና ስም እየታሸ ይገኛል::ዋና አላማው በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የሚነሱ ተልእኮዎችን በማኮላሸት በሕወሓት ቁጥር ስር ለማዋል እንዲሁም ሕወሓት ደርግን በመደምሰስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለውለታ እንደሆነ በማሳየት ለሕወሓት የበላይነት ስኬት የታቀደ ስልጣና እና ግምገማ ነው::
Minilik Salsawi's photo.
የቀድሞውን ወታደራዊ ስርኣት ለመጣል የአሁኑን የሽምቅ ሽብራዊ መንግስት ለማንገስ በበረሃ ትግል የተሳተፉት የኢሕኣዴግ ድርጅቶች በሃገሪቱ የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው::በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስራትን ለማስፈን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ታግለን ህዝባዊ ነጻነትን እናረጋግጣለን በማለት ጫካ የተደባለቁት ድርጅቶች የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት ታላቋን ትግራይን እፈጥራለሁ ያለውን ሕወሓት የትግሉ ስኬት ሲከሽፍበት ኢሕዴንን እና ኦሆዴድን በመንተራስ ተረማምዶ ለስልጣን ከበቃ 25 ድፍን አመታትን አስቆጠረ::ከዘላለም ባርነት የአንድ ቀን ነጻነት አግኝቶ መሞት እንዴት የተሻለ መሆንን መገንዘብ ብስለት ሲሆን ለሌሎችን ከባርነት የማላቀቅ አንዱ መፍትሄ ነው::
የኢሕዴንን እና የኦሕዴድን የትግል አስታውጾ ላማኮላሸት እና ከታሪክ ሂደት መስመር ለማሳት የተጠቀመባቸው ዘዴዎች እና ወታደራዊውን እና የደህንነቱን ተቋም በአንድ ብሄር በማጠር አባል ድርጅቶቹ እና አባላቱ መላወሻ እንዲያጡ ሲሰራ በአደባባይ ታይቷል::ከአቶ ታምራት ላይኔ የፖለቲካ ጠለፋ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ቁጥራቸው ይህ ነው የማይባሉ የኢሕዴን ታጋዮች እና ካድሬዎች በተለያዩ የወንጀል ልጣፎች ከያሉበት ተጠልፈው ወደ ሞት እስር እና ስደት ተግዘዋል:: የኦህዼድ አባላትንም እንዲሁ በመጥለፍ በፖለቲካዊ የኦነግ ታርጋ በማሰር በመግደል እና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች በማሸት አንደበታቸውን አሽጎታል:: ይህ የሕወሓት ስራ ማንም የሚያውቀው እና ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው:: የአማራውና የኦሮሞው ህዝብ ኢሕዴን/ብኣዴንን አይተው ኦሕዴድን አይተው እንጂ ለሕወሓት ሲሉ የእትዮጵያን መሬት በመምራት አልተባበሩም ስለዚህ የብኣዴን እና የኦሕዴድ አመራሮች እና ካድሬዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ ትግሉ ሕወሓት ብቻ የመራው ያደራጀው ያሸነፈው አለመሆን እና የድርጅቶቹም ድርሻ እኩል መሆኑን ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳ

No comments:

Post a Comment