)
የጋራ ሀገር አለን ብሎ የሚያምን ሰው ፥ ለ ዲሞክራሲ ግንባታ እታገላለሁ ብሎ የሚያስብ አካል እና የዛ አካል ውላጅ ፥ ሃሳብን በነፃነት ስለመግለፅ በሚደሰኩርና የዜጎች መብት ይከበር ዘንድ ( እንዲከበር ) ነው የምታገለው የሚል ኣካል ፥ ትንንሽ ( ደቃቃ) ሃሳቦች ያስፈሩታል ብለን አንገምትም ። ስለ እኩልነት እያወራን እራሳችን እኩል መሆን ያቃተን ከሆንን ፥ የማንፈቅደውን ለመሆን የምንታገል ነን ማለት ነው !
ስለ ሃገራችን ያገባናል ያሉት ሰዎች የሚያደርጉት ትግል ሁሉ ያገባናል ። እንኳን ስለ ሃገራቸው ገዷቸው በርሃ የገቡት ፥ የምንግዴዎቹም አካሄድ ያገባናል ። ምንግዴዎቹ ከጥፋታቸው ይመለሱ ዘንድ ከመናገር ፥ ከማጋለጥ እና ህዝብን ከማሳወቅ ዝም አንልም ፥ የገደዳቸው የፖለቲካ ሂሳቡ ምናባዊ ( complex imaginery ) ሲሆንባቸው የተሻለ የምንለውን እንናገራለን ። ቢያንስ ቢያንስ የምንኖርበት ሃገር ታሪክ ፥ የዕለት ተዕለት የህይወት ሂደቱ ( ውጣ ውረዱ ) የሚያሳየን እሱን ነው ። ትሞክራለህ ፥ ይበላሽብሃል ፥ ደግመህ ትሞክራል ፥ አሁንም አልሰራም ይልሃል ፥ ትገመገማለህ ፥ ሙከራውን ወደሚሰራ አቅጣጫ ሊወስድ የሚያስችል አቅም የነጠፍክ ከሆነ የተሻለ ይመለመላል ። ትግል እምነት አይደለም ። እምነት ላይ ክርስቶስ አለ እሱን ሲከተል ኖሮ አርጅቶ የሚሞት ትውልድ አለ ፥ ለአዲሱ ትውልድም ያው የቅድሙ ( የቀደመው ) ክርስቶስ አለ ። ይህ የሚመረመር ፥ የሚፈተን ፥ የሚጠየቅ ነገር ስላይደለ « ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው » የሚለውን እያነበብክ ፥ ተስፋ እና ፍቅር ሰንቀህ ፥ አምነህ ትኖራለህ ። ፖለቲካ ግን እንዲያ አይደለም ። ፖለቲካ የመሪዎች ታሪክ ነው ለዚህም ነው ታላቁ ሆመር በጣፈው ኢሊያድ ላይ
<< history remember kings but not soldiers>> የሚለው ። ስለዚህ ስለ ክሽፈት ስናወራ ከመሪ ጋ ይያያዛል ማለት ነው ። መሪዎች መስማትም መቀበልም ያለባቸው ነገር አለ ስንል ከዚህ ተነስተን ነው ። ውድቀቱም ሆነ ድሉ መጀመሪያ የነሱ ነውና !
ለምሳሌ ጦርነቱን ለማሸነፍ በግለሰብ ደረጃም ቢሆን ወርደው ማሰብ የሚጠቅም ከሆነ ማድረግ ። የቡድን አስተሳሰብ ካልሰራ በግለሰብ ደረጃም ቢሆን የሚሰራ ሃሳብ መፍጠር ። በኢሊያድ ላይ ኦዳይሰስ እና አገማምኖን ይህንን ብለው ነበር
Agamemnon: Achilles is one man!
Odysseus: Hector is one man! Look what he did to us today!
Agamemnon: Hector fights for his country! Achilles fights only for himself!
Odysseus: I don’t care about the man’s allegiance, I care about his ability to win battles!
Odysseus: Hector is one man! Look what he did to us today!
Agamemnon: Hector fights for his country! Achilles fights only for himself!
Odysseus: I don’t care about the man’s allegiance, I care about his ability to win battles!
በዘራቸው ሳይሆን በችሎታቸው ጦር ሊመሩ የሚችሉ ታጋዮችን ማቀፍ ፥ ማሳተፍ እና ወደፊት ማምጣት ወሳኝ ነው ። እንዳንናገር የምትፈልጉትን አካሎች ግን ” በእርግጥ እኛ እናንተን ኣይደለንም !” እንናገራለን !! ለውጥ እስኪመጣ ድረስ! መናገር የሚጎዳውን ትግል ፥ ዝምታ አያድነውም!!!! ሹክሹክታ እንዲያገግም አያደርገውም ። የጀርባ ወሬ አያተርፈውም ። እንደውም የሚገለው እሱ ነው
No comments:
Post a Comment