Wednesday, May 4, 2016

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ከ2 ሺ በላይ ወጣቶች ታሰሩ

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ከ2 ሺ በላይ ወጣቶች በፀረ ሽፍታ ልዩ ሃይል ታድነው ታስረዋል።
* ” ወደ ተከለከለ የደን ቦታ ገብታቹሃል ” የሚል ምክንያት ለእስራቸው መነሻ ተደርገዋል።
ከ2 በላይ ወጣቶች ታድነው የታሰሩት በቓፍታ ሑመራ ወረዳ የሚገኙ በባህላዊ መንገድ ወርቅ የሚወጣባቸው ቦታዎች ነው።
የወርቅ የሚወጣበት ቦታ ከዓዲ ጎሹ እስከ ዓደባይ የሚገኝ ሰፊ መሬት ከሸረ ወደ ሑመራ ሲጓዙ ወደ ሰሜን ኣቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን እስከ ኢትዮ_ኤርትራ ድንበር የሚያዋስን የተከዘ ዳርቻዎች የተዘረጋ ነው።
ኣፈሳው የተካሄደው በጠበቖ(ኣንድ ወጣት ሙቶ የተገኘበት)ገዛ ግርማይ፣ መቓብር ዓንደማርያም፣ እነይ ቕበፅኒ ከሚባሉ በወርቅ የበለፀጉ የተከዘ ደንደሶች ነው የተያዙት።(ከዚ በፊት 85 ወጣቶች የታገቱበት ቦታ ነው።) በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች ከፀረ ሽፍታ ልዩ ሃል እንዳመለጡ ታውቀዋል።
ቦታው ወርቅ የሚወጣበት ብቻ ሳይሆን ታጣቂዎች ከኤርትራ እየተሻገሩ በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች ኣግተው የሚወስዱበትና የሚገድሉበትም ጭምር ነው።
የፀረ ሽፍታ ሃይሉ በወጣቶቹ ላይ ዘመቻ የጀመረው ከ17 እስከ 20 /08/08 ዓ/ም ሲሆን ከ2 ሺ በላይ ወጣቶች ኣድኖው ከተያዙ በኋላ በሑመራ ከተማና ሌሎች 13 ቀበሌዎች በተሰሩ ግዝያዊ እስር ቤቶች እንዲታሰሩ ኣድርገዋል።
የዞኑ ሃላፊዎች ወጣቶቹ ለመቅጣት በርካታ የዳኞች መድበው በዘወቻ መልክ የተፈረዱባቸው ሲሆኑ እያንዳንዱ ወጣት ከ700 ብር እስከ 1500 ብር እየከፈልክ ልትወጣ ትችላለህ ተብለዋል። ወጣት ገብርሃንስ ይልማና(700 ብር) ሃለቃ ሓጎስ ገብሩ(1000 ብር) እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።
መክፈል ያልቻሉ ወጣቶች “ከቤተሰቦቻቹ ኣስልኩ ወይም ተበደሩ” እየተባሉ እየተገደዱ ይገኛሉ። ወርቅ በማውጣት ስራ የተሰማሩ ወጣቶች ድሆች ሲሆኑ በኣገራቸው ስራ ለመስራት ዕድል ያላገኙ፣ ወደ ኣውሮፓ ለመኮብለል ቤተሰቦቻቸው ለሕገ ወጥ ደላሎች(የህወሓት ባለስልጣናት ሸሪኮች) ለሚከፈል ብር ኣቅም ያነሳቸው ናቸው።
ወደ ቦታው ሲመጡም ሁለት ዕድል ግምት ውስጥ ኣስገብተው ነው።
ሀ) ወርቅ የማግኘት ተስፋና ወርቁን ሽጠው ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸውን መርዳት
ለ) ከኤርትራ በሚሻገሩ ታጣቂዎች ታግተው ወደ ኤርትራ ተወስደው በባርነት መማቀቅ ነበር።
ሌላ ያልጠበቁት ሶስተኛ ኣደጋ ደሞ
፦ በህወሓት መሪዎች ታድነው መያዝ፣ መታሰርና በገንዘብ መቀጣት የሚለውን ነው።
በኣሁኑ ሰዓት የህወሓት መሪዎች ተግባር ወጣቱ ከህገ ወጥ ደላሎች ጋር በመመሳጠር ከመላ ትግራይ ከተሞችና ገጠሮች ወጣቶች እያማለሉ ለሊብያ መላክና ወላጆቻቸው ተገድደው የሚልኩት 14000(መቶ ኣርባሺ ብር) ተካፍለው መብላት ነው።
ሰሞኑ በማይካድራ ያጋጠመ ምሳሌ የህወሓት ባለስልጣናት በዚ ሕገወጥ ተግባር እጅ እንዳለባቸው ያመላከተ ነው። በኮብላይ ወጣቶች ” ልጆቻችን መልስልን ኣለበለዚያ እናጋልጠሃለን” ተብሎ በወላጆች የተደወለለት ብርሃነ ኣሸብር የተባለው ኣስከውላይ “…በሉ እርማቹ ኣውጡ እኔ የትም ኣታገኙኝም። የኔ ብር ያልቀመሰ የትግራይ ባለስልጣን የለም። ስለዚ ኣርፋቹ የሚጠበቅባቹ ብር ክፈሉ። ካልሆነ ልጃቹ ወደ ኩላሊት ነጋዴዎች ይላካል…” ሲል ዝተዋል።
በሉ እዩልኝ ! እነዚህ ባለስልጣናት በትግራይ ያለው ድሃው ወጣትም በ13 ግዝያዊ ማጎርያዎች ኣግተው በመያዝ ያለ ደላላ ብር ውለድ እያሉ እያስጨነቁት ይገኛሉ።
ወጣቱ ትውል እሳት ትርያንግል ሰርቶ እየለበለበው ይገኛል።
የህወሓትና ባለ ስልጣናት=====> ህገ ወጥ ደላሎችና ኩላሊት ነጋዴዎች(ስደት)====> ከኤርትራ የሚሻገሩ ታጣቂዎች ናቸው።


2 comments on

No comments:

Post a Comment