Thursday, May 12, 2016

በአርባምንጭ ከ20 በላይ የመንግስት ወታደሮች ተገደሉ | መንግስት ከኤርትራ የተላኩብኝን “አሸባሪዎች” አሰርኩ ይላል | ግንቦት 7 ጥቃት ፈጸመ???

በአርባ ምንጭ ከተማ ድንገት ታጣቂዎች በሰነዘሩት ጥቃት ከ20 በላይ የመንግስት ወታደሮች መገደላቸውን መዘገቡን ተከትሎ መንግስት ማምሻውን በኢቢሲ በኩል ባስተላለፈው መረጃ ከኤርትራ መንግስት በኩል የተላኩብኝን አሸባሪዎች ደቡብ ክልል ጥቃት ከማድረሳቸው በፊት ያዝኩ አለ::
የኤርትራ መንግስት በኡጋንዳ በኩል በአየር አሳፍሮ እንዲሁም በኬንያ በኩል እንዲያልፉ በማድረግ በደቡብ ክልል ጥቃት ለማድረስ ሲሉ በቁጥጥር ስር አይውያለሁ ቢልም ኢሳት በሰበር ዜናው በአርባ ምንጭ ከተማ ከ20 በላይ የመንግስት ወታደሮች ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል ሲል ዘግቧል::
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በሶሻል ሚድያ በኩል “ወያኔ በአርባ ምንጭ የተሰነዘረበትን ድንገተኛ ጥቃት በተዘዋዋሪ ለማማን ተገዷል።” በሚል መንግስት በኢቢሲ በኩል የሰጠውን መግለጫ በመንተራስ አስተያየታቸውን እየሰጡ ባለበት በዚህ ወቅት ያዝኳቸው ያላቸውንና ከኤርትራ በኩል ተላኩብኝ ያላቸውን ታጣቂዎች ምንም ጉዳት ሳያደርሱ ያዝኩ ማለቱም እያነጋገረ ነው::
ኢሳት በዘገባው
“የአካባቢው ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት ታጣቂዎቹ ባደረሱት ድንገተኛ ጥቃት 20 የመንግስት ወታደሮች ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል። ከተገደሉት መካከል የአካባቢው ወታደራዊ አዛዥም ይገኝበታል። የተኩስ ልውውጡ ለረጅም ሰአታት የቀዬ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ህክምና ተወስደዋል። የመንግስት የጸረ ሽብር ግብረሃይል ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ከኤርትራ የተንቀሳቀሱ ሃይሎች በሞያሌ በኩል ወደ አርባምንጭ ጫካ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ገልጿል። መንግስት በቁጥጥር ስር የዋሉና የተገደሉ ታጣቂዎች መኖራቸውን ቢገልጽም ፣ በአሃዝ ከመግለጽ ተቆጥቧል። ይሁን እንጅ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ድንገተኛ ጥቃቱን የፈጸሙት የታጠቁ ሃይሎች፣ ጥቃቱን ካደረሱ በሁዋላ ከአካባቢው ተሰውራል። ይህን ተከትሎም ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የከተማው ሰዎች እየታፈሱ ተወስደዋል። ”

No comments:

Post a Comment