(ዘ-ሐበሻ) ከ9 ሰዓታት በፊት ፕሬስ ቲቪ የተባለው የዜና አውታር አይሲስ በሊቢያ 16 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ገደለ የሚል ዜና አስነብቦ ነበር:: በድረገጹ ላይ የወጡት ፎቶዎች በሙሉ ባለፈው ዓመት አይሲስ 28 ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያንን የገደለባቸው መሆኑን ብዙዎችን ሲያጠራጠር ቆየ:: በተለይም ታላልቅ ሚዲያዎች ይህን ዜና እንዴት ሊዘግቡት አልቻሉም? የሚለው አንጋጋሪ ነበር:: የፕሬስ ቲቪን ዘገባ ሁለት የ እንግሊዝ ታብሎይዶች ቢለጥፉትም በመጨረሻም ይህን የግድያ ዜና የዘገበው ፕሬስ ቲቪ ዜናውን ከድረገጹ ላይ አጠፋው::
ፕሬስ ቲቪ ዜናውን እንደዘገበ የኮዩኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ በቲቪ ወጥተው በተገደሉት ኢትዮጵያውያን ዙሪያ የተሰማቸውን ሃዘን መግለጻቸውና ፕሬስ ቲቪም ወዲያውኑ ከድረገጹ ዜናውን ማንሳቱ ከበስተጀርባው ምን እንዳለው ወደፊት የሚታይ ቢሆንም ብዙዎች ወደ ዘ-ሐበሻ በመደወል ዜናውን እንድናረጋግጥላችሁ በጠየቃችሁን መሰረት ሞቱ የሚለው ዜና የተረጋገጠ አይደለም::
ወደ ሊቢያ በተለይም ባንጋዚ እና ትሪፖሊ የሚኖሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ጋር ስልክ ደውለን የሰሙት ነገር እንዳለ ጠይቀን እነርሱም ጋር ያገኘነው ምላሽ ምንም የሰማነው ነገር የለም የሚል ነው::
ዜናው እስከሚጣራ በ ት ዕግስት ጠብቁ::
No comments:
Post a Comment