Friday, October 20, 2017

የሕወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ሰሞኑን ትግራይን ለመገንጠል መምከሩ ተገለጸ፣ በሕዝባዊ ተቃዎሞዎች ላይ ሕወሓት የላካቸው የደህነት አባላት ጥፋትና ሕዝብ ከሕዝብ የማጋጨት ስራ እየሰሩ ነው




  
By ሳተናውOctober 20, 2017 14:52   
(ህብር ሬዲዮ -ላስ ቬጋስ) በአገሪቱ እየተስፋፋ የመጣው ሕዝባዊ ተቃውሞ ማየልን ተከትሎ ሕወሓት በትግራይ መቀሌ ላይ ሰሞኑን የማዕካላዊ ኮሜቴ በስብሰባዎ ዛሬ ድረስ በድርጅቱ ፕሮግራም የሚገኘውን የትግራይ መገንጠል አጀንዳ ላይ ውይይት ማድረጉንና ሕዝቡን ስለ ትግራይ መገንጠል እያወያየ መሆኑ ተገለጸ።
የአረና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አምዶም ገ/ስላሴ እንደገለጸው ሰሞኑን የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አጀንዳ አድርጎ የተወያየበትን የትግራይ መገንጠል ጉዳይ ሕዝቡን ትግራይ ብትገነጠል ምን ይመስላችሁዋል እያሉ ወረዳና ቀበሌ ድረስ ባለው መዋቅር ወርዶ እየተጠየቀ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
ሕወሓት ከ42 ዓመት በፊት ሲመሰረት በ6 ወር ውስጥ የትግራይ ትግሪኛ ሪፐብሊክ እመሰርታለሁ ማለቱን አስታውሶ ዛሬ ከ42 ዓመት በሁዋላ አጀንዳው ለምን ተነሳ ሲል ይጠይቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሕወሓት አገዛዝ አገሪቱ ላይ ያሰፈነው ከአንድ ብሄር ተውጣጣ የገዢ ቡድን በጉልበት መግዛት የማይችልበት ደረጃ ሲደረርስ የአገቱን አንጡራ ሀብት ሲዘርፍ ከኖረው የቀረውን አሟጦ፣ህዝብን ከሕዝብ ለ26 ዓመት ሲያስፋፋ በኖረው የዘር ፖለቲካ አጋጭቶ፣ አገሪቱን በታትኖ ትግራይን ለመገንጠል ወደ መጨረሻው ደረጃ እየተቃረበ መሆኑን ጃዋር መሐመድን ጨምሮ የተለያዩ አክቲቪስቶችና የተቃዋሚ መሪዎች ለህብር በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ በጥያቄ ቀርቦላቸው መመለሳቸው አይዘነጋም።
በቅርቡ በሶማሌና በኦሮሚያ መካከል ዘርን መሰረት አድርጎ ሶማሌ ልዩ ሀይልን ተጠቅሞ በንጹሃን ላይ የከፈተው ጦርነት ከ200 መቶ በላኢ ንጹሃን ሲገዱ ከ140 ሺህ በላይ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችበዘራቸው ምክንያት ሲፈናቁ የህወሓትን የተልዕኮ የዘር ግጭት ለማስነሳት የሚሰሩት የሶማሌው ክልል ፕሬስዳንት አብዲ ኢሌ ቃል አቀባይ 350 ሶማሌዎች መፈናቀላቸውን መጥቀሳቸው ይታወሳል።
ስልጣን ወይም ሞት ብሎ የተነሳው ሕወሓት ለ26 ዓመትት አማራና ኦሮሞን ለማጋጨትና እርስ በእርስ በጥርጣሬ እንዲተያዩ ለማድረግ የሰራው ሴራ ሁሉ እየከሸፈ መሔድ ተቃውሞውን ተከትሎ በደህነት አባሎቹ አንዱ አንዱ ላይ ጥቃት እንደወሰደ ለማድረግ እና የህዝብ እልቂት ለመጋበዝ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል።
ጋዜጠና ሙሉቀን ተስፋው ከሰሜን ሸዋ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ እንደዘገበው ትላንት ጥቅምት 9 ቀን 20110 ዓመተ ምህረት በሰሜን ሸዋ ዴራ ላይ አማራና ኦሮሞውን ለማጋጨት የሕወሓት ተላላኪዎች <<አማሮች ሊወሯችሁ መጡ>> ብለው እስከመቀስቀስ ቢሄዱም ሁለቱም ወንድማማች ሕዝቦች ከጥዋቱ ጀምሮ በመራህቤቴ እና በዴራ ለሕዝባዊ ተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሲሆን በአገዛዙ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ሶስት ንጹሃን ተገለው አራት ቆስለዋል።

No comments:

Post a Comment