Saturday, October 7, 2017

የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል ግጭት እልባት አለማግኘቱ ተጠቆመ


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |


 
በሁለቱ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት አሁንም እልባት አለማግኘቱ ተጠቆመ፡፡ ከስፍራው እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደጠቆሙት፣ በተለይ ከከተማ ወጣ ብለው በሚገኙ የድንበር አዋሳኝ ቦታዎች ላይ አሁንም መጠነኛ ግጭት እየተከሰተ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ስርዓት በማገልገል ላይ የሚገኙት መገናኛ ብዙኃን፣ ግጭቱ መቆሙን እየተናገሩ ቢሆንም፣ መረጃዎች ግን የግጭቱን ሙሉ በሙሉ አለመቆም እየጠቆሙ ናቸው፡፡
የኦሮሚያ-ሶማሊ ግጭት ተፈናቃዮች (File Photo)
ጉዳዩን አስመልክቶ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እያካሔደ የሚገኘው የስርዓቱ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት፣ ሆን ብሎ ግጭት የሌለ ለማስመሰል እየሰራ ይገኛል፡፡ ግጭቱ ከሚከሰትበት ስፍራ የሚወጡ መረጃዎች እንደጠቆሙት፣ በአሁን ሰዓት ዕቃ ጭነው ወደ ውጭ የሚወጡም ሆነ ከውጭ የሚገቡ መኪኖች ድንበር ላይ ቆመው ይገኛሉ፡፡ መኪኖቹ ለመቆም የተገደዱት ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ሲሆን፣ የጫኑት ዕቃ እየተራገፈም ፍተሻ እንደሚደረግባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለወትሮው በድንበር እና በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ብቻ የነበሩ የፍተሻ ኬላዎች፣ በአሁን ሰዓት በየቅርብ ርቀቱ ላይ በብዛት እንደሚስተዋሉ የዓይን እማኞች ይገልጻሉ፡፡ በዚህም የተነሳ በየቦታው ፍተሻ እንደሚደረግ ከመረጃዎች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በመጠኑም ቢሆን በድንበር ቦታዎች ላይ እየተከሰተ ያለው ግጭት ወደ ውጭ ለሚወጡም ሆነ ከውጭ ለሚገቡ መኪኖች ፈታኝ በመሆኑ፣ መኪኖች ዕቃ ጭነው ለበርካታ ቀናት ለመቆም ተገድደዋል፡፡ (BBN News)

No comments:

Post a Comment