Tuesday, October 31, 2017

የትግሬ ነፍስ ከሌላው ይበልጣልን?


By ሳተናውOctober 30, 2017 17:02
    
ሙሉቀን ተስፋው
ሦስት ትግሬዎች ነቀምት ላይ መገደላቸውን ተከትሎ አገር ቁልቢጥ ሆናለች፤ ነገሩ በሦስት የሚቆም ቢሆን ባልከፋ! ገና ከአስቀያሚው ዘመን ዋዜማ ላይ መሆናችን ለፈርዖኖቹ አልታያቸውም፡፡
የኦሮሞን ወጣት በለው ጨርሰው እያለ የትግሬ ወታደር በአምቦ ሲገድል አላወገዙም፤ የዐማራ ስጋ በከማሽ የጅብ ቀለብ ሲሆን የትግሬ እስካልሆነ ድረስ ምንም አይደለም፡፡ በወልቃይትና ጠገዴ ዐማራን ገድለው በመኪና አስከሬን የሚጎትቱ እነዚህ አውሬዎች ዛሬ ሦስት ተጋሩዎች መሞታቸውን ተከትለው አገር ይያዝ ኡኡ እያሉ ነው፡፡ እኔ የማዝነው አንድ አስተዋይ ሽማግሌ በማጣታቸው ነው፤ መጪው ጊዜ የከፋ መሆኑን የሚነግራቸው፡፡
ግብዞቹ በጎንደር የእርቅ ኮንፍረንስ ለማካሔድ አስበናል እያሉን ነው፡፡ የወልቃይትና የራያ ዐማሮች ዐማራነታቸው ሳይከበር ዕርቅ አይደለም ከሚቀጥሉት መቶ ዓመታት በኋላ እንኳ የተገነባው የጥላቻ ግንብ መፍረስ የሚችል አይደለም፡፡ መቼም አይፈርስም! መጪው የዐማራ ትውልድ አባቱንና ወንድሙን ማን እንደገደለበት እርስቱን ማን እንደቀማው ከ‹ሀ ሁ› ፊደል ጋር እኩል እየቆጠረ ያድጋል፡፡ ከዚያ ትውልዱ በራሱ የሚያደርገውን ያውቃል፡፡



No comments:

Post a Comment