Sunday, October 29, 2017

ብሔራዊ ባንክ በአዲስ መመርያ ለግል ኩባንያዎች የውጭ ብድር ዋስትና ሊሰጥ ነው


  
By ሳተናውOctober 29,  
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መመርያ በኤክስፖርት የተሰማሩ አገር በቀልና የውጭ ኩባንያዎች፣ ከውጭ የፋይናንስ ምንጮች ብድር የሚያገኙ ከሆነ ዋስትና እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡
ብሔራዊ ባንክ ሰሞኑን ባፀደቀው መመርያ በተለይ በወጪ ንግድ ተሰማርተው የውጭ ምንዛሪ የሚያመነጩ ኩባንያዎች፣ ከውጭ አበዳሪዎች ብድር የሚያገኙ ከሆነ  ለመጀመርያ ጊዜ ዋስትና እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡
መመርያው ለውጭ ምንዛሪ ብቻ ሳይሆን ለማሽኖችና ለጥሬ ዕቃዎች ጭምር  ዋስትና እንዲያገኙ የሚያስችል ነው፡፡ የአዲሱን የብሔራዊ ባንክ መመርያ በወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችና ኢንቨስተሮችች ‹‹መልካም ዜና›› ብለውታል፡፡
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ፊርማ የወጣው ስድስት ገጾች ያሉት መመርያ አሥር አንቀጾች አሉት፡፡
የግል ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚያካሂዷቸው ሰፋፊ ኢንቨስትመንቶች የፋይናንስ ምንጫቸው የአገር ውስጥ ባንኮች ብቻ ሆነው ቆይተዋል፡፡
በተወሰነ ደረጃ በተለይ ዓለም አቀፍ ብራንድ ባላቸው ኩባንያዎች የሚተዳደሩ ባለኮከብ ሆቴሎች ብሔራዊ ባንክን እያሳወቁ ብድር ሲፈቀድላቸው ነበር፡፡ ይኼ ግን በሁለቱ አበዳሪና ተበዳሪዎች መካከል በሚደረግ ስምምነት ላይ የተመሠረተ እንጂ፣  ብሔራዊ ባንክ ዋስትና ሰጥቶ አያውቅም፡፡
በየፋይናንስ አቅርቦት አማራጭ መጥፋት በተለይ በማኑፋክቸሪንግ፣ በሰፋፊ እርሻዎች፣ በቱሪዝምና በአገልግሎት መስጫ ተቋማት የተሰማሩ፣ ነገር ግን የውጭ ምንዛሪ ማመንጨት የሚችሉ ተቋማት ለዓመታት ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡
በመጨረሻ ብሔራዊ ባንክ ይኼንን አዲስ መመርያ ቁጥር 47/2010 በማፅደቁ፣ በኤክስፖርት በተሰማሩ ኩባንያዎች መነቃቃት መፍጠሩ ታውቋል፡፡
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ባለሀብት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አንድ በወጪ ንግድ የተሰማራ የውጭ ምንዛሪ ማመንጨት የሚችል ኩባንያ ከውጭ የፋይናንስ ተቋም ጋር ተደራድሮ ያቀረባቸው የመደራደሪያ ነጥቦች ተቀባይነት ካገኙ ብድር ሊያገኝ ይችላል፡፡ ይኼ ኩባንያ ዓለም አቀፍ ብራንድ ያለው ባለመሆኑ (አገር በቀል ኩባንያ) በመሆኑ ብቻ፣ አበዳሪው ተቋም ለሚሰጠው ብድር የአገሪቱን ዋስትና ይፈልጋል ብለዋል፡፡ ነገር ግን ብሔራዊ ባንክ ዋስትና የማይሰጥ በመሆኑ ብድሩ ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል፣ አሁን ግን መመርያው በመውጣቱ የውጭ ምንዛሪ ማመንጨት የሚያስችል ሥራ ላይ የተሰማራ ኩባንያ፣ ከውጭ ብድር አግኝቶ ሥራውን ሊያስፋፋ የሚችልበት አማራጭ በመፈጠሩ ‹‹መልካም ዜና›› ነው ሲሉ ባለሀብቱ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፎሬን ኤክስቼንጅና ሪዘርቭ ማኔጅመንት ዳይሬክተር ወ/ሮ የኔሐሳብ ታደስ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አዲሱ መመርያ ለአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ላይ ለተሰማሩ ኩባንያዎች ጭምር የሚሠራ ነው፡ 





    

No comments:

Post a Comment