Friday, October 20, 2017

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የኤርትራውያን ሥደተኞች ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ



ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የኤርትራውያን ሥደተኞች ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ


ሳተናው
By ሳተናው
October 20, 2017 14:59










144
Shares
 Share
 Tweet
 Email
 Share



ጥቅምት 20, 2017

•ቪኦኤ ዜና

ዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት እኤአ ካለፈው መጋቢት 2017 ወዲህ ከአስራ አምስት ሺህ በላይ ኤርትራውያን ስደተኞችን ተቀብሎ ትግራይ ክልል ውስጥ ማስፈሩን አስታወቀ።

ዋሺንግተን ዲሲ — ዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት እኤአ ካለፈው መጋቢት 2017 ወዲህ ከአስራ አምስት ሺህ በላይ ኤርትራውያን ስደተኞችን ተቀብሎ ትግራይ ክልል ውስጥ ማስፈሩን አስታወቀ።ዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግሥት የሥደተኞችና ከሥደት ተመላሶች አስተዳደር እና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን /ዩኤንኤችሲአር/ ጋር በቅርበት በመተባበር አዲስ ገቢ ኤርትራውያን ሥደተኞችን ኢንዳባጉና ከሚገኘው የሥደተኛ መቀበያ ማዕከል በክልሉ ወደሚገኙ አራት የሥደተኛ ካምፖች አጓጉዘዋል።

ትግራይ ክልል ሽሬ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ቢሮ ኃላፊ ሐታብ ኻሊድ በሰጡት ቃል በአሁኑ ጊዜ በየቀኑ አንድ መቶ ሰዎችን ተቀብለን በማስፈር ላይ ነን ብለው የሚገቡት ሥደተኞች ቁጥር በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት መጨመሩን እንደሚጠቁም ገልጸዋል ።
በወጡ ኦፊሴላዊ አሃዞች መሰረት ባለፈው የአውሮፓውያን 2016 ኢትዮጵያ የገቡ ኤርትራውያን ሥደተኞች ቁጥር ሃያ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አሥራ አምሥት ሲሆን እአአ 2017 ደግሞ እስካሁን በአለው ጊዜ የገቡት ቁጥር ከሃያ ሺህ መብለጡን ይጠቁማል። አብዛኞቹ ሥደተኞች ወጣቶች መሆናቸውንና /አይኦኤም/ ካሰፈራቸው መካከል አርባ ስድስት ከመቶው ከአሥራ ሥምንት እስከ ሃያ አራት ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል

No comments:

Post a Comment