Saturday, October 21, 2017

ከጎንደር ወጣቶች በድጋሚ የተላከ ጥብቅ የመጨረሻ ማሳሰቢያ



  
By ሳተናውOctober 21, 2017 08:15

1k Shares
Share
Tweet
Email
Share

#በመላው አማራ ክልል ከፍተኛ የህዝባዊ እምቢተኝነትና መራራ የተጋድሎ እንቅስቃሴ ምክንያት ከአገልግሎት ውጭ የተደረገው የወያኔ የገቢ መሰብሰቢያ ዳሽን ቢራ የደረሰበትን ኪሳራ በሌላ በረቀቀ መንገድ ለማስተካከል ያሰበው “አልሸሹም ዞር አሉ” እንደሚሉት አባቶቻችን ስሙን ቀይሮ “ባላገሩ ቢራ” ብለው ለገብያ ቢያቀርቡም ከኪሳራ ማዳን አልቻሉም።
አሁንም ይሆናል ባሉት መንገድ የህዝብ የሆነ እ ና በህዝብ የተመሰረተውን የፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ክለብን አርማ ስም ለዳሽን ቢራ ፋብሪካ “ጃኖ” ቢራ በሚል አዲስ መጠሪያ ለማስተዋወቅ ዛሬ ጥቅምት 11/02/2010 ቀጠሮ መያዙን በሀዘን ዜና ሰማን።
ውድ የፋሲል ከነማ ተጫዋቹች እና አመራር ኮሚቴ አባላት ፣ደጋፊዎች እንዲሁም ለኮንሰርቱ ተጋባዥ ወጣት አርቲስቶቻችን (ለያሬድ፣ ደጉ,፣ሳሚ ፣ዳንና ፣ ብስራት፣ ሱራፌል )ሁላችሁም የህዝብ ልጆች መሆናችሁንና ህዝብ ሲበደል ሲገፋ ሲሰደድ የስቃይ ስሜቱ ስሜታችሁ እንደሚሆን እናምናለን። ሆኖም ግን አሁን ያለንበት ሰአት ያላገናዘበ እንዲያውም ብዙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በዚህ አስቀያሚ ስርአት በግፍ ደማቸው በየጎዳናው እየፈሰሰ በአደባባይ በጠራራ ፀኃይ እየተገደሉ ፣ እየተጋዙ፣ ፣እየተደበደቡ ግን የህዝባዊ(ተጋድሎ እና,የእምቢተኝነት) ,ድምጾች በቆራጥነት ወደ በአደባባይ ወተው እየሰማን እያየን ባለንበት ቅጽበት እንዲህ አይነት አይን ያወጣ ዳንኪራ የማድረግ ሞራሉ በለለው ህዝብ መካከል ለመገኜት መወሰናችሁ ይቅር የማይባል እና ከእናንተ የማየረጠበቅ ታሪካዊ የሆነ ስህተት ነው። ደግሞም በቅርቡ ስንት ወጣቶች ለነጻነት በተዋደቁባት ጎንደር ከተማ ላይ ኮንሰርት ማድረግ ፈጽሞ የማይታሰብና የህዝብን ስሜት ወደ ሌላ ብስጭት የሚከት በመሆኑ እንድትተውት አጥብቀን በቅድሚያ እንመክራለን፡፡
ስለሆነም እውነተኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች መሆናችሁን በዚህ አጋጣሚ እንድታስመሰክሩና ሃገራዊ ግዴታችሁንም በፍጥነት በማያሻማ መልስ አንዘፍንም በማለት እንድትወጡ እናሳስባለን። ነገር ግን ይሄን ሳታደርጉ ቀርታችሁ በሚደርሰው አደጋም ይሁን ችግር የነጻነት ትግል ተሳተፊዎች ሃላፊነት የማይወስዱ መሆኑን ከወዲሁ አስረግጠን ለመንገር እንፈልጋለን፡፡
ከህዝብ ልጆች !!
አንድነት ሃይል ነው!!

No comments:

Post a Comment