Saturday, October 28, 2017

ቤኒሻንጉል በሎደዴሳ ቀበሌ በሎጅጋንፎይ ወረዳ ካማሽ ዞን እስካሁን 25 ሰዎች ተገድለዋል።

   
የቤኒሻንጉል ጉዳይ አሳቢ ነው።
ፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው ቢገባም ችግሩ በጣም የከፋ ነው እያሉ ነው።ነቀምት ሆስፒታል በአስከሬን መጨናቅቁን የሆስፒታል ምንጮች እየጠቆሙ ነው።

ቤኒሻንጉል በሎደዴሳ ቀበሌ በሎጅጋንፎይ ወረዳ ካማሽ ዞን እስካሁን 25 ሰዎች ተገድለዋል።በአንድ ጉዜ ብቻ 48 ቁስለኞች ወደ ነቀምት ሆስፒታል ተወስደዋል።የአምስት አመት ህፃን ከቁስለኞች መካከል ትገኛለች።
የጎጃም ህዝብ ድረስልን እያሉ ነው። ለአማራ ብዙሀን መገናኛ።ተደጋጋሚ ደውለን ስልክ አይነሳም።ለክልሉ ብአዴን ቅርንጫፍ አሳውቀናል።
ቤቱ የተቃጠለው የወረዳው ዋና አስተዳድሪ፣ ምክትል፣ ድርጅት ጉዳይና አስተዳደርና ፀጥታ እያሉ ነው።

“በየአመቱ የመኸር ወቅት ዝርፊያ ይጀምራሉ።ዘንድሮም ከሶስት ቀን በፊት ጀምረው ሲዝቱ ሲዘርፉ ነበር የሰነበቱት።
አሁን በዚህ ሰዓት እንኳን ሰሊጥ ያለበት ቦታ ቤታችንንም ሰሊጣችንም እያቃጠሉት ነው”…ይህንን ያለኝ ከግድያ አምልጦ የወረዳው ከተማ የገባው ወጣ ነው።
“የማውቀው ምኒችል የሚባል ወጣት ገበሬ ነበር።ትራክተር ነበረው።እርሱን ትናንት ገድለውታል።አሁን በጠዋቱ ብቻ ሰባት ሰው ተገድሎ ተገኝቷል” ሌላ የወረዳው ነዋሪ ነው።

No comments:

Post a Comment