Tuesday, October 31, 2017

ለመሆኑ በብርሃን ጸዳል የተሽቆጠቆጠችው፤ ከሀገረ ቻይና እና ከብራዚል ጋር ዓለምዐቀፍ ተሸላሚዋ ዘመነኛዋ ትግራይ ግራጫ ጸጉር አላትን?


By ሳተናውOctober 30, 2017 23:32

 
ከሥርጉተ – ሥላሴ 31.10.2017 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ።/
„ … እንሆም፣ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፣ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል፣ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሷል።
/ መጽሐፈ ምሳሌ ተግሣጽ ምዕራፍ 24 ከቁጥር 30 እስከ 31/“
እንደ በር።
ሥርጉተ ሥላሴ
ሥርጉተ ሥላሴ
በመጀመሪያ ጥናቱንና መቀነቱን 40 ዐመት ሙሉ በዕንባ ክርትት ለሚሉ ለኢትዮጵያ እናቶች እንዲሰጥልኝ አምላኬን እማጸነዋለሁ። በሥጋ የተለዩትንም ወገኖቼ ሰማዕትነታቸውን ፈጠሪዬ ይቀበልልኝ ዘንድም እማጸነዋለሁ።
በማስከትል … ወደ ዋናው ጉዳዬ ከመሄዴ በፊት ግን የአዋዜ አዘጋጅ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ የሰሞናቱን የአማራን የተደራጀና የታቀደ ጭፍጨፋ አስመልክቶ የሠራው ዜና እጅግ ውስጥን የተረጎመ፤ ሩቅ አሳቢና መንገድ ጠራጊ ዕድምታ ስለነበረ እጅግ አድርጌ ላመሰግነው ፈቀድኩኝ። ደፋር፤ ጥልቅ ትንታኔ ነው። ቅርብ – ከሩቅ ጥቃትን ያዋደደ ነው። ዓለም – ዓቀፋዊ ሰቅጣጭ የጭካኔ ዕውነታዎችን፤ ሁኔታዎችን በምልሰት የቃኘበት መንገዱ ብጡል ነው። አማራ እኮ ሐገር አልባነቱ ተውጆበታል። የከፈለው ደም ከንቱም ሆኗል። ስለሆነም የአዋዜ የንጽጽሩ የአምክንዮ አቅሙ አንቱ ነው። ለህሊና ቅድመ መሰናዶ ልዩ ተቋምም ነው። ለአማራ ሥነ – ልቦናዊ አኃቲነትም በኲራት ነው። አጭር ግን ልቅም ያለ፤ ልቁን የአማራን ዬዘር ጥፋት ትልም በጥልቀት የመረመረ፤ በስፋት ያስተዋለ፤ በውስጥነት የተቀበለ፤ የጉዳቱ ልክ በአትኩሮት እንዲታይ ፈር ቀያሽ የሆነ – መጸሐፍ ነው። ተባረክ! 

No comments:

Post a Comment