Tuesday, October 10, 2017

አስደንጋጭ አደጋ ጎንደር ላይ ደረሰ

አስደንጋጭ አደጋ ጎንደር ላይ ደረሰ
መስከረም 30 2010
በመገንባት ላይ ያለ የጎንደር ዮኒቨርስቲ/ማራኪ ካምፓስ ህንፃ ተደርምሶ እጅግ በጣም ብዙ ሠራተኞች በዛሬው ማክሰኛ እለት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ለመወጣጫ የተገጣጠሙት የእንጨት ርብርብ በመደርመሳቸው በስራ ላይ ያሉ ወገኖች ከ6 እስከ 9 ፎቅ ከሚደርሰው ህንፃ ላይ ለመውደቅ ተዳርገዋል። ብዙወች ለሞትና ለከባድ ጉዳት መዳረጋቸው ከቦታው ተነግሮናል። የጉዳቱ ሰለባወች ብዙወቹ የቀን ሰራተኞች ናቸው። ቸቸላ ሆስፒታል በህዝብ ተጨናንቋል። ጥበቃዎች አናስገባም ብለዋል፡፡
...
የህንፃ ተቋራጩ አፍሮ ጽዬን ኮንስትራክሽን ሲሆን ባለቤቱም ሲሳይ የሚባል የትግራይ ባለሃብት መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ጎንደር ያሉ የንግድና የመንገድ እንዲሁም የህንፃ ስራወች ለትግራይ ተወላጆች ልዩ ቅድሚያ እንደሚሰጥባቸው ከአሁን በፊትም ከነማስረጃው ዘግበንባቸዋል።በህዝባችን ላይ ስለደረሰው ጉዳት በጣም እያዘንን ለተጎዱት አፋጣኝ ህክምና እንዲያገኙ ወገንተኝነቱ የተሰማቸው የህክምና ባለሞያወችን ትጋት ይሻል። ስለ ህንፃ ተቋራጩና ስለ ደረሰው ጉዳት ዝርዝር ሁኔታ እያጣራን ነው።
AsnakewAbebe

No comments:

Post a Comment