Tuesday, October 10, 2017

በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ድንበር ላይ በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ድጋፍ እንዲደረግ ፕሬዝዳንቱ ጥሪ አቀረቡ።

           

ዶ/ር ሙላቱ ተሾመImage copyright Getty Images
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ለሁለቱ ምክር ቤት አባላት ባደረጉት ንግግር የመንግሥትን የ2009 አፈፃፀም እና የ2010 ዕቅድ አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ የተፈናቀሉ ዜጎች መልሰው እንዲቋቋሙ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው በግጭቱ ምክንያት ለተፈጠረው ጉዳት ተጠያቂዎችን ከህግ ፊት ለማቅረብ እየሰራን ነው ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ተሾመ እንዳሉት የምርጫ ማሻሻያ ህጉ በ2012 ለሚካሄደው ምርጫ ተግባራዊ ይደረጋል።
ከዚህም በተጨማሪም የመንግሥት የንብረት ግዢ ስርዓት፣ የመሬት አቅርቦት እና የመዘጋጃ ቤቶች የስራ አፈፃፀም ደካማ ሆኖ ታይቷል፤ የፀረ-ሙስና ትግሉም በ2010 ዓ.ም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ላለፉት ሶስት ዓመታት ሃገሪቷ የወጪ ገቢ ንግዱን ለማመጣጠን ከፍተኛ ፈተና ገጥሟት ነበር።
ለዚህም ምክንያቱ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች መጠን መቀነስ ነው ተብሏል። ለቡና፣ ሰሊጥ፣ ቅመማ-ቅመም እና ለአበባ ምርት ትኩረት በመስጠት የንግድ ሚዛኑን ለማስጠበቅ እንደሚሰራ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተናግረዋል።
መንግሥት ለለውጥ የገባው ቃል ከምን ደረሰ?
በ2009 ዓ.ም ሃገሪቷ በ10.9 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግባለች፤ ይህም ፈጣን የሆነ ኢኮኖሚ እንዳላት ያሳያል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ ለሁለት ሚሊዮን ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን በንግግራቸው አስታውቀዋል።
ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ላይ ትኩረት በማድረግና የታክስ ስርዓቱን በማዘመን የሃገሪቷን ገቢ ለማሳደግ እንደሚሰራም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment