Saturday, October 21, 2017

መንግስት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ይቅርታ ጠይቀው ከእስር ቤት እንዲወጡ ሽማግሌዎችን ላከ


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

1,31K Shares
(ዘ-ሐበሻ) በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ሕወሓት መራሹ መንግስት ካለአግባብ በግፍ ጠርጥሮ ያሰራቸውን ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን እንዲፈታ በተለይ ከአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ግፊት እየተደረገበት ባለበትና ሃገር ቤት ያለውም ሕዝባዊ አመጽ እየተቀጣጠለ መንግስትን ወደ መጣል እየደረሰበት ባለበት በዚህ ወቅት መንግስት መረራ ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡ ሽማግሌዎችን መላኩን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

እንደምንጮቻችን ገለጻ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ያለው ሕወሓት መራሹ መንግስት ባለፈው ሳምንት አራት ሽማግሌዎችን ፕሮፌሰሩ ወደታሰሩበት እስር ቤት የላከ ሲሆን ሽማግሌዎቹም መራራ ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡና ይቅርታ የመፈረሚያ ወረቀት አቅርበውላቸዋል:: ፕሮፌስር “መረራ ይቅርታ አልጠይቅም የታገልኩለት ሕዝብ ሕዝብ ያስፈታኛል” በማለት ሽማግሌዎቹን እንደመለሷቸውም የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል::
ፕርፌሰር መረራ ይቅርታ አልጠይቅም  ካሉ በኋላ ሽማግሌዎቹ ለማግባባት ሙከራ ያደረጉ ቢሆንም ሳያሳካላቸው ተመልሰዋል::
በአሁኑ ወቅት በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እየተደረጉ ባሉ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ሕዝቡ ከሚያነሳቸው አንደኛው ጥያቄ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ሲሆን ስር ዓቱ በቀጥታ ለሕዝቡ ምላሽ መስጠት ሲገባው ታሳሪዎችን ይቅርታ ጠይቃችሁ ውጡ ወደሚል የተለመደ ተልካሻ ሴራው እየገባ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ይናገራሉ::

No comments:

Post a Comment