Saturday, October 7, 2017

በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል የተመደቡ ተማሪዎች ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ ተናገሩ


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |


በአዲሱ የትምህርት ዘመን በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል የተመደቡ የሁለቱ ብሔር ተወላጅ ተማሪዎች ለደህንነታቸው እንደሚያሰጋቸው ተናገሩ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል የተፈጠረው ግጭት እንደሆነ ተማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ የ12ኛ ክፍል አጠቃላይ ፈተና ወስደው ካለፉት ተማሪዎች መካከል በሺዎች የሚቆጠሩት በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዋል፡፡ ሆኖም በሁለቱ ክልሎች መካከል ያለው እና አሁንም መቋጫ ያልተገኘለት ግጭት ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተሉ እንቅፋት እንደሚሆንባቸው የኦሮሞ እና የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጅ ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ ምላሽ የሰጠው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ ለተማሪዎቹ ደህንነት አደጋ የሚሆን ነገር እንደሌለ ቢገልጽም፤ ተማሪዎቹ ግን አልተቀበሉትም፡፡ ግጭቱን ተከትሎ በተማሪዎች ላይ ሊፈጠር ይችላል ተብሎ የሚታሰበውን የደህንነት ችግር በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ጽ/ቤቱ ይህን ቢልም፣ የተማሪዎቹን ስጋት ግን መቅረፍ አልቻለም፡፡
በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል መካከል የተፈጠረው ግጭት ለብዙዎች የደህንነት ስጋት ሆኖ እንደቀጠለ ነው፡፡ በተለይ ከመማር ማስተማር ስራው ጋር በተገናኘ ተማሪዎችም ሆኑ አስተማሪዎች የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ ባለፈው ሳምንት የጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ በሁለቱ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ለደህንነታቸው እንደሚያሰጋቸው መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በሌሎች ስራዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎችም፣ በግጭቱ የተነሳ ከሁለቱ ክልሎች ጠቅልለው መውጣታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡  (BBN NEWS)

No comments:

Post a Comment