Friday, October 27, 2017

የአጋዚ ወታደሮች ላይ ጊንጪ ጥቃት ተሰንዝሮ ሁለቱ ተገደሉ::

ኢሳት መረጃ- - ጊንጪ
በጊንጪ ነዳጅ ማደያ አከባቢ በነበሩ የአጋዚ ወታደሮች ላይ ጥቃት ተሰንዝሮ ሁለቱ ሲገደሉ: ሁለት ወታደሮች ቆስለው ወደህክምና ማዕከል መወሰዳቸን የደረሰን መረጃ አመለከተ:: ጥቃቱን የፈጸመው ማን እንደሆነ አልታወቀም::

 ተቃውሞው በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ቀጥሎ መዋሉ፣ በተለያዩ ተቋማት ዩኒቨርሲቱ ተማሪዎች በአምቦ ለተገደሉ ወገኖቻቸው ተቃውሟቸውን ማሰማታቸው፣  የደረሰን መረጃ አመለከተ::    በአምቦ የተጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ወደምትገኘው የሆለታ ከተማ ተዛምቷል። በአሁኑ ሰአት በከተማዋ ህዝባዊ አመጽ ተቀጣጥሏል።የከተማዋ መንገዶችና አውራ ጎዳናዎች ሙሉ በሙሉ ዘግተዋል ፣ የስራ እንቅስቃሴም ተቋርጧል።ዝርዝር መረጃውን ተከታትለን እናቀርባለን።

No comments:

Post a Comment