Monday, October 30, 2017

የዳንጎቴ ሲሚንቶ ተሽከርካሪዎች አምስት ከባድ የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ተቃጠሉ



By ሳተናውOctober 29, 2017 10:59
 
በኢትዮጵያ ባለአክሲዮኖች ተገንብቶ በሚያዝያ 2009 ዓ.ም. ምርት የጀመረው ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር በገጠመው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከማክሰኞ ጥቅምት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ማምረት ማቋረጡ ተሰማ፡፡
ታማኝ የዜና ምንጮች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ተቃውሞ የሚያሰሙ ወጣቶች ማክሰኞ ጥቅምት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በሆለታ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ በመግባት የፋብሪካውን ምርት አስተጓጉለዋል፡፡ ወጣቶቹ ፋብሪካው ሥራ እንዲሰጣቸው ወይም ደመወዝ እንዲከፍላቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ፋብሪካው ሥራውን ማከናወን ባለመቻሉ ከተጠቀሰው ዕለት ጀምሮ ምርት እንዳቆመ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የሐበሻ ሲሚንቶ ዋና ሥራ አስፈጻሚ  መስፍን አቢ (ኢንጂነር) ፋብሪካው በገጠመው የፀጥታ ችግር ሥራ ማቆሙን ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡ ከ20 የማይበልጡ ከአካባቢውና ከሌላ ቦታ የመጡ ግለሰቦች በፋብሪካው የማዕድን ማውጫ አካባቢ በፈጠሩት የፀጥታ ችግር፣ ፋብሪካው ሥራ ለማቆም መገደዱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡
‹‹ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከክልሉ መንግሥትና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር እየሠራን ነው፤›› ብለዋል፡፡
ሐበሻ ሲሚንቶ በግንባታ ወቅት ለ650 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንና ወደ ምርት ከገባ በኃላ 500 ተጨማሪ የሥራ ዕድል መፍጠሩን የጠቀሱት ምንጮች፣ በሥራ ቅጥር ወቅት ለአካባቢው ተወላጆች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡ በፋብሪካው የማዕድን ማውጫና በፋብሪካው ውስጥም የተለያዩ ሥራዎችን በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ የአካባቢው ወጣቶች እንደሚሠሩ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሐበሻ ሲሚንቶ ከፍተኛ የማኔጅመንት አካላትና የዳይሬክተሮች ቦርድ በጉዳዩ ላይ እየመከሩ ነው፡፡
የሐበሻ ሲሚንቶ በ30 መሥራች ባለአክሲዮኖች በ2000 ዓ.ም. የተመሠረተ ሲሆን፣ የባለአክሲዮኖች ቁጥር 16,000 ደርሷል፡፡ የሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካን ለመገንባት የአገር ውስጥ ባለአክሲዮኖች የሚፈለገውን የካፒታል መጠን ለማሟላት ባለመቻላቸው፣ 51 በመቶ ድርሻ ለደቡብ አፍሪካው ፒፒሲ ኩባንያ መሸጣቸው ይታወሳል፡፡ ከብዙ ትግል በኋላ በ140 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ተገንብቶ ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ተመርቆ ምርት ጀምሯል፡፡ ፋብሪካው በዓመት 1.4 ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ የማምረት አቅም አለው፡፡
ምንጮች ለሪፖርተር እንደገጸሉት፣ ፋብሪካው በገጠመው የፀጥታ ችግር ላይ ለመምከር የደቡብ አፍሪካው ዋና ባለአክሲዮን የሆነው ፒፒሲ ኩባንያ ወኪሎቹን ወደ አዲስ አበባ ልኳል፡፡ የቦርድ አባል የሆኑት የፒፒሲ ተወዮች፣ የሐበሻ ሲሚንቶ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትና ለፋብሪካው ብድር ያቀረቡ ባንኮች ኃላፊዎች ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በጎልደን ቱሊፕ ሆቴል ስብሰባ ሲያካሂዱ መዋላቸው ምንጮች አስረድተዋል፡፡ የሐበሻ ሲሚንቶ ማኔጅመንት አባላት ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሔ ለመፈለግ እስካሁን በስብሰባ መጠመዳቸውን ገልጸዋል፡፡
በተያያዘ ዜና የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ተሽከርካሪዎችአምስት ከባድ የጭነት ማመላለሻ  በእሳት መጋየታቸው ታወቀ፡፡ ሦስቱ ተሽከርካሪዎች የተቃጠሉት ባለፈው ሳምንት በገብረ ጉራቻ ከተማ በተፈጠረ ሁከት ሲሆን፣ ሁለቱ ደግሞ ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በአምቦ ከተማ በተካሄደ ተቃውሞ መቃጠላቸው ታውቋል፡፡ የአምቦ ከተማ የኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጋዲሳ ደሳለኝ ዓርብ ጥቅምት 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት የ10 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች የሚከሰቱ ግጭቶች በክልሉ ኢንቨስት

No comments:

Post a Comment