Monday, October 23, 2017

የሙስናዋን ንግስት አዜብ መስፍንንና አባይ ፀሀዬን የረሳ ዘመቻ








የትግሬ ወያኔ ቡድን የፀረ ሙስና ዘመቻ ብሎ በጀመረው የፉገራ ጨዋታ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ያመጣሉ ብሎ በሚጠረጥራቸውና በዘር ማንነታቸው ጭምር የማይፈለጉትን ባለስልጣናት ማጎሪያ አድርጎታል በታሰበውና በታቀደው መሰረት የነዚህ ታሳሪ ባለስልጣኖች ቦታ ለትግራይ ተወላጆች ተመቻችቶላቸዋል የሙስናዋን ንግስት አዜብ መስፍንን የማያካትት የሙስናውን ንጉስ አባይ ፀሃዮን ያልጨመረ እነ ጀነራል ክንፈ የረሳ የሙስናና ሌቦችን የመያዝ ዘመቻ ቀልድ ነው
ሀገሪቱን በዘረፋ ባዶ ያደረጉት የትግሬ ወያኔ ባለስልጣናት ከሃገሪቱ ማዕድን እስከ እንጅራ ንግድ በቁጥጥራቸው ስር አድርገው ሊላው ኢትዮጵያዊ ነጋዴ አቅም በማሳጣት ተስፋ በማስቆረጥ መተንፈሻ ካሳጡት ግዜያት አልፍዋል እነሱ ያለ ግብር ይነግዳሉ የፈለጉትን ከውጪ ሃገራት ያስገባሉ የፈለጉትን ያለ ምነም ከልካይ ከሃገሪቱ ያስወጣሉ ሀገሪቱ ላይ ነግዶ ማትረፍ የማይታሰብ ሆንዋል ለቀሪው ኢትዮጵያዊ በሀገሪቷ ውስጥ የሚወጡ ማንኛውም ጨረታ አጫራች ሕወሃት(ወያኔ) ተጫራቹም አሸናፊም ሕወሃት(ወያኔ) ነው፡፡

ስርዐቱ አይን ያወጣ ዘረፋም መለያው ነው ሲያስፍልግ ህዝብን በመናቅ ጠፋ በሚል ሽፋን ፊት ለፊት ዘረፋን መፈፀም አንዱ ባህሪያቸው ነው 88 ኮንዶሚንየም ጠፋ 420 ቶን ብረት ጠፋ 2 መርከብ ቡና ጠፋ 650 ቶን ስኳር ጠፋ የማይነግሩን ጉድ የለም፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እነሱን መታገል መተባበር አለበት ሀገሪቱን አዘቅት ውስጥ ከተዋታል

አምባ ገነኑ ስርዐት (ወያኔ)ህሕዋት አዲሱን አመት የኢትዮጵያን ህዝብ የከፍታ ዘመን ብሎ ቁልቁል ሊጎዳው ዝግጅቱን አጠናቋል በ2010 እስርና አሳሩን ለማብላት በሚል አጀንዳ ነድፎ መንቀሳቀስ ጀምሯል፡፡ ይህ የሀገርና የህዝብ ጠላት የሆነ ስርዐት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚከሰቱ ፖለቲካዊ ሆነ ማህበራዊ አልያም ኢኮኖሚያዊ ቀውሰ በዋነኛነት ተጠያቂ ነው፡፡


ኢትዮጵያ ሃገራችንንና ህዝባችንን በየአቅጣጫው እያደማ እያቆሰለ ተስፋ እያሳጣ ለመግዛት ቢሞክርም አሁን ግዜው አይፈቅድም በወያኔ የአገዛዝ ዘመን የስርዐቱ የጭካኔ ብትር በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤት በር እያንኳኳ አስነብቷል ከወያኔ የጭካኔ ብትር ያመለጠ ዜጋ የለም አሁን ግን ይህ ሁሉ መከራ ሊያበቃ እንዳለ ተስፋ ሰጪ ነገሮች ይስተዋላሉ፡፡

የወያኔ ባለስልጣናት የግፍ ፅዋው ሞልቶ እርስ በርሳቸው እንካን መግባባት አቅቷቸው ቋንቋቸው መደበላለቅ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ከዚ ቡሃላ ከመጣው ለውጥ ፈላጊ ወጣት የተነሳ ሀገርን ቆርሶ ለባዕድ መሸጥ የሚታሰብ አይሆንም፤ ዜጎች ሃሳባቸውን በመግለፃቸው ብቻ እስር ቤት ማጎር አይሞከርም፤ ኢትዮጵያዊው ወጣት ሃገር ውስጥ ተስፋ በማስቆረጥ ለአረብ ሀገራት በባርነት መልክ መሸጥ ፍፁም አይቻልም፤ የሀገርና የህዝብ ንብረትን መዝረፍ ይቆማል፤ ዜጎችን በዘር ሀረጋቸው ምክንያት ማፈናቀል ማሰር ማሰቃየት ያበቃል፤ የአንድ ዘር የበላይነት ታሪክ ይሆናል፡፡ አሁን ከወያኔ ፊት የቆመው ትውልድ አገዛዙን ጠራርጎ ሊወስደው የተነሳ ማዕበል ነው፡፡

በመከፋፈል የጥላቻን ዘርን በመዝራት የሚታወቀው ስርዐት በአዲስ አመት አዲስ ማንነት ብሎ በመደጋገም እንፋቀር ፍቅር ፍቅር ብሎ ቢያላዝንም የተናገረው ቃል ሁለት ቀን እንኳን ሳይሞላው የስርዐቱ እውነተኛ ማንነት ፈንቅሎ ወቷል፡፡ ሲገል ሲያስር ሲያሰቃይ የኖረ ማንነት እንዴት ያልተፈጠረባትን ሊኖር ይችላል፡፡

ድምፃዊ ቴድሮስ ካሳሁን ኮንሰርት አዘጋጅቶ መዝፈን ሙዚቃውን ማስመረቅና መሰል ጉዳዮችን ማድረግ መንግስት ያለበት ሀገር ቢሆን ህገመንግስታዊ መብቱ መሆን ሲገባ ይህ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ሀገሩን ወዳድ ሀገሪቱ በአምባገነኖች በአሳሪዎችና በፈቺዎች እጅ ስር በመውደቅ ይህንን መብቱን በተደጋጋሚ አቷል፡፡

ስርዐት ያልገባው ነገር በማፈን ማሸነፍ አይቻልም በጉልበት መግዛት ፍፁም ከባድ ነው ገለህና አስረህ አሰቃይተህ ጥላቻ የከተትክበትን ህዝብ ደግሞ እንዲወደኝ አደርጋለሁ በማለት ስለ ፍቅር ማውራት ቁስሉን መነካካት ነው፡፡እንዲሁም ዘመን በተቀያየረ ቁጥር መሪ ቃል ይዞ መምጣት እራስን ማታለል ነው፡፡ የወያኔ ባለ ስልጣናት የልተረዱት ባረጀ ፕሮፓጋንዳ የዘመኑን ወጣት አዲሱን ትውልድ ማታለል ከባድ እንደሆነ ነው የስርዐቱ መሪዎች የሚያስቡትም የሚከውኑትም ነገር ሁሉ ያረጀ ነው ዛሬ ላይ አይሰራም እራሳቸውም አስተሳሰባቸውም አርጅቷል ለዛም ነው በዚህም ግዜ በጠመንጃ መግዛት እንደሚቻል የሚያምኑት
ይህም ሆኖ ሀገርን በመዝረፍ ስራ ላይ የተጠመዱት የገዢው ቡድን መሪዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ የከፍታ ዘመን ለእነርሱ ግን የዝቅታ የውድቀት ግብአት መሬታቸው የሚፈፀምበት ግዜ እንደሆነ መንፈሳቸው ያረጋገጠላቸው ይመስለል፡፡ ሕውሃት(ወያኔ) የሚፈልጋት ኢትዮጵያ የጥላቻ ጥግ የሰፈነባት ዘር ከዘር የሚባላባት፣ መግባባት የጠፋባት ፣ ውድቀቷ የፈጠነ ከአንድ አካባቢ በስተቀር የቀሩት ክልሎች ገሃነም ውስጥ ሆነው የሚኖሩባት በርሃብ፣ በስራ አጥነት፣ በኑሮ ውድነት፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ ቀውሶች የምትለበለብ ሃገር እንድትሆን ነው ዋነኛ አላማው፡፡


ለዚህም ነው ይህ እውነት የበራለት ኢትዮጵያዊ ህውሃት ወያኔ ሃገርን ገዝግዞ ሳይጨርስ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በአንድነት ተነስቶ አልገዛም ያለው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እነሱን መታገል መተባበር አለበት ሀገሪቱን አዘቅት ውስጥ ከተዋታል፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

No comments:

Post a Comment