Friday, October 20, 2017

ሰሜን ሸዋ አማራውና ኦሮሞው በአንድነት ቆሞ ወያኔን እየተፋለመ ነው


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

396 Shares
ሙሉቀን ተስፋው
አገዛዙ በዴራ ሰሜን ሸዋ ዐማራና ኦሮሞን ለማጋጨት የሸረበው ሴራ ከሸፈ፤ የ3 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
በሰሜን ሸዋ ዴራ ትናንት የዐማራና የኦሮሞ ተወላጆችን ለማጋጨት በአገዛዙ የተሸረበው ሴራ ሙሉ በሙሉ የከሸፈ ሲሆን በአገዛዙ ኃይሎች የሦስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ ትናንት ጥቅምት 9 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋት ጀምሮ በዴራና በመራህቤቴ የተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተካሒደዋል፡፡
በተቃውሞው 7 ሰዎች በጥይት ተመትተው የሁለቱ ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ አንደኛው መራቤቴ ሆስፒታል ቢደርስም መትረፍ ባለመቻሉ የሟቾች ቁጥር ሦስት ደርሷል፡፡ ቀሪዎቹ 4ቱ ደግሞ በሪፈራል ወደ ደብረ ብርሃን ሆስፒታል ተልከዋል፡፡
የአገዛዙ ኃይሎች ከቱቲ የመጡ ዐማሮች ኦሮሞዎችን ሊያጠፉ ነው ብለው ቢሰብኩም ‹‹ሁላችንም አንድ ነን›› በሚል ከመራህቤቴ፣ ብቸናና ዴራ የተሰባሰቡ ዐማሮችና ኦሮሞዎች ዛሬም ከአገዛዙ ኃይሎች ጋር ሲጋፈጡ መዋላቸውን ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የመራህቤቴ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአጋዚ ወታደር እንደተከከበ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

No comments:

Post a Comment