„…ሰው ሁሉ ዕውቀት አጥቶ ስንፎአል፣ አንጠረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሳ አፍሮአል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስል ውሸት ነውና፣ እስትንፋስም የላቸውምና። እነርሱም ምናምንቴና የቀለድ ሥራ ናቸው፤ በተጎበኙ ጊዜ ይጠፋሉ።“
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 51 ከቁጥር 17 እስከ 19)
ህም!
መቼም እንዲህ ዓይነት ሰብዕና ፈጣሪ አምላክ ከሚሰጥ ሳይፈጠሩ መቅረት በስንት ጣዕሙ። ከቃለ ምልልስ ዕይታ እንደ አዳመጥኩት፤ ዬጦማርውያኑንም መንፈስ እንዳነበብኩት የህዝብ አመኔታ ማጣት የአያ እንቶኔውን የሰብእና ቀዳዳ እንዲህ መበራከት ደጎስ ያለውን እጅ ዬያዘ ስለመሆኑ ያመለከታል። ይገርማል፤ ቅርጥምጣሚ ታማኝነት ማጣት የእውነት ስለእርግማን ነው። የፖለቲካ ወቅታዊ ጉዳዮችን ተንታኙ ጋዜጠኛ ኤርምያሰ ለገሰ „የበረከት ነገር“ በሚል ዕርዕስ ካሰፈረው ውስጥ …
„ስለ በረከት ስምዖን አቋም እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም። እሱም ቢጠዬቅ ስለራሱ እርግጠኛ ሆኖ መግለጽ የሚችል አይመስለኝም። በህይወቴ ካጋጠሙኝ አለቃዎች ውስጥ የቴርሞሜትሩ መለኪያ ከዜሮ መቶ፣ ከመቶ ኔጋቲብ በደቂቃ ውስጥ ሲለዋወጥ ያዬሁት በርከትና በረኸት ብቻ ነው።“ የሃይለ ቃላቱን ስንኞች ሲደመሩ እንደ አንድ ሙሉዑ ሰው አይዋ እንቶኔን ለማዬት ይቸግራል። ለራሳቸውም ታማኝ ለመሆን እንኳን አቅም የሌላቸው መሆኑን የተዘቀዘቀ ዕጣ ነው። በዛ ላይ ቋሚ የሆነ የመወሰን ጸጋም የራቃቸው ሰው መሆናቸውን ደግሞ በአያ እንቶኔ ላይ እንደ አንድ በሙሉ ዕድሜ ያለ ጎልማሳ ሰው ሰብዕና ለዛውም የፖለቲካ ሰው ሲታይ ሚዛን ያልፈጠረለት ሰብዕና መሆኑን ያመላክታል። እግረ መንገዱንም የግብታዊነት ክትባታዊ ተፈጥሮንም ያመሳጥራል ። አያጣል ነው ….
ኦ! አምላኬ።
እኔ እኒህ የተንኮል ቦንዳ ከዬት እንደ ተፈጠሩ ይገርመኛል። ቤተሰቦቻቸው እጅግ ደጎች ነበሩ – በማህበራዊ ኑሮ። አባታቸው ጭራሽም ይኑሩ አይኑሩ የማይታወቁ የግንባታ ጥበብ የነበራቸው የታፈሩና የተከበሩ ነበሩ። እማ ብሬም ቢሆኑ የማህበራዊ ኑሮ አንበል ነበሩ። በዛን ጊዜ እኔ ታዳጊ ወጣትም እያለሁ፤ ወጣትም ሆኜ፤ በተጨማሪም በዚህው የወጣትነት ዘመኔ ዬሥራ ሃላፊነት ላይ ሆኜ ከአንባጅኔ እስከ ጨዋሰፈር የነበሩትን ኤርትራውያን ቤተሰቦች ጋር በደስታውም በሃዘኑም ቤተሰቦቻችን ይገናኙ ነበር። …. የአባ ተስፋማርያም፤ የአባ ገረማሪያም ጎኔ፤ የአባ ተክሌ፤ የአባ ገ/ህይወት (የሴራው ቦንዳ) ወላጅ አባት፤ የጋሼ ማህሪ ጉዳይን በምልሰት ስቃኝ ከዛ ቅናዊ መንፈስ አፈንግጦ እንዲህ ያለ የከሰለ እንክርዳድ ጉድ መፈጠር አሁን ድረስ ሚስጢሩ አልገባሽ ይለኛል። ያን ጊዜ ትንሽ በስጨት በማለት ይታማ የነበረው ባለጋራጁ ጋሼ ማህሪ ቢሆንም እሱም ከቤቱ ያለፈ በሌላው ላይ የሚጭነው ምንም ገራፊ ህፃፅ አልነበረበትም። ቅን ሰውም ነበር። የጋሼ ማህሪ ባለቤቱ እትዬ ሽታዬ ደግሞ እጅግ የታቦት ያህል እርጋታ አብዝቶ የሰጣት ስለነበረች ሚዛኑን ታስጠብቀው ነበር። እትዬ ሽታዬ ነፍሴ ነበረች። በተለዬ ሁኔታም ታቀርበኝ ነበር። ልጆቿ ልዩ ነበሩ። የአባ ተ/ማርማያም ይሁን የአባ ተክሌ ልጆችም ምን ይወጣላቸዋል። እነ እንገዳ … ታዲያ ይህን ስምየለሽ ባለቦንዳው ሴራዊ ዬተፈጥሮ ገጸ-ባህሬ አቶ በረከት መብራቱ ከዬት አመጡት ይባላል? ከማንስ ተማሩት? ከወዴትስ አመረቱት?
አሁን አሁን እኔ ሳሰላው አቶ ሴራ በነፍሱ ቢጠዬቅ የት ተፈጠርክ? የትስ አደክ? የትስ ተማርክ? የትስ የጸላዬ-ሰናይነት ዲቁና ተቀበልክ? የትስ የሴራውን ጨላማዊ ኮርሶች አጠናቀቅክ? የትስ የሴራውን ሦስት ጉልቻህን አህዱ አልክ? የትስ ሸመገልክ ቢባል ያለጥርጥር ከአቶ በረከት ገ/ህይወት ህሊና ይላል።
የሆነ ሆኖ በመጠጊያ አልባነትን የመሸገው ውሳኔያቸው እንደ መስቀል የደመራ ባላ የመጨረሻው አወዳደቅ አቅጣጫውን መተርጎም ወይንም መተንበይ ያልተቻለውም ከዚህ ጉድጓድ፤ ዝንቅ የሸር ቤተኝነታቸው ይመስለኛል። የአስተያዬቶችን የአዬር ላይ የጉባኤ ዕድምታ ስመዝነው በሚገርም ሁኔታ ውስጠ – ወጥ የሆነ አሉታዊ ዕድምታ አለው። መሃከነ።
በሌላ በኩል በበጎ ጎኑ ባዩት ወገኖቼ ወይንም ድርጅቶች ላይም ወቀሳ ነገር አንብቤያለሁ። ለእኔ በበጎ ጎኑ ያዩት ወገኖች እኔ ባዬሁበት ቅርጻዊ ምስል ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ይህን ስል የእሳቸው ከወያኔ ሃርነት ትግራይ መልቀቂያ ማቅረብ ይዘታዊ አድርጎ ማዬት በፍጹም ሁኔታ የሚቻል አለመሆኑን ግን እኔ የማምንበት ጭብጥ ነው። ይዘታዊ ትርፍ የለውም ስል ተፍጥሯዊ ውስጣዊነት በድርቅ ከመመታት አያመልጥም ለማለት ነው። ግልጽነት ተፈጥሮው ያልሆነ ሰው ለዬትኛውም አካል እንደ አንድ ተጨማሪ ጉልበት ሊታይ ስለማይገባ። ስለሆነም ለእኔ ቅርፃዊ ወይንም ቅብ ነገር ነው ባይ ነኝ። ይህ ማለት ግን የጠቀሜታ ፍርፋሪ ወይንም እንጥፍጣፊ ለወቅቱ የትግል ሙቀት አይኖረውም ማለት አይደለም። አሁንም ይህን ስል ግን የመልቀቂያ ጥያቄው እርግጠኝነት በተመለከተ እኔ እምከተለው የጋዜጠኛ እና የወቅታዊ ፖለቲካ ተንታኙን የኤርምያስ ለገሰን ሃሳብን ነው።
የሴራው ቦንዳ ቅርፃዊ ወይንም ቅባዊ ጠቀሜታው።
- ለውጪ የሎቢ ሥራ የገዢው ፓርቲው የወያኔ ሃርነት ትግራይን መዋቅርን መሰንጠቅ ወይንም መተርተር ለማሳመን እንደ አንድ ማውጫ (Reference) ለመጠቀም ይረዳል። የተነቃነቀ መንጋጋ መሆኑን እንደ ማለት …
- የነፃነት ትግሉን ወላፈን ያማሙቃል። ያው ሃሳቦች ወዲህና ወዲያ ሲንሸራሸሩ እግረ መንገዱን የሰውን የግንዛቤውን አድማስ ያሰፋል፤ ተሳትፎውንም በተወሰነ ደረጃ ይጨምራል። ሞቅ ሞቅ ሲል ተሳታፊው በርከትከት ይላል … አድማጭም እንዲሁ ይጨምራል።
- በወያኔ ሠፈር ያሉትን የወያኔ የጀርባ አጥንት አና ደጋፊዎች፤ የታላቋ ትግራይን ህልመኞች አከርካሪ ደግሞ ደህና አድርጎ ንጦ ያናጋል ወይንም ይጎሳስማል፤ የውስጥ ለውስጥ ወጣዊ ሃዲዱን ንፋስ – ገብ ያደርገዋል። እንዳትረሱ ወገኖቼ አሁንም እርግጥ ከሆነ የመልቀቂያው ጥያቄ ….
- የተንኮሉን ዬስቅስቅ ማማረቻ ካንፓኒ ከወትሮው
No comments:
Post a Comment