Tuesday, October 31, 2017

አይነኬ የህወሓት ጀነራሎች!!! በኮንትሮባንድ የሰከሩ፣የደም ገንዘብ!!!


     
      
ክፍልአንድ | / ፂዩን ዘማርያም

ላንባው ተነቃነቀ!!!

የሳኦል መንግሥት ወደቀ!!!


‹‹በፊት በፊት እኛን መመርመር አይቻልም” ያሉ የዘመናችን የመንግስት ተቋማትን አይተናል፡፡ ይሄ እንግዲህ የፖለቲካ አይነኬዎች መፈጠራቸውን ያረጋግጥልናል፡፡ መሬት የዘረፉ እጃቸውን ቸብ ቸብ ተደርገው፣ ተቀጡ ተብለው ወዲያው ይለቀቃሉ፡፡ አንድ ሞባይል የመነተፈ ግን አደገኛ ቦዘኔ ተብሎ ከ2 ዓመት በላይ ይታሰራል፡፡ የፖለቲካ ኃይልና የዘረፋ ኃይል ውህደቱ ከፍተኛ ነው፡፡ “ይሄ የኔ ሰው ነው፤ አትንካው” የሚባልበት የአይነኬዎች ስርአት ነው የምለው ከዚህ አንፃር ነው፡፡›› ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

የህወኃት የጦር አበጋዝ  መንግስት፣“ይሄ የኔ ዘር ነው፤ አትንካው” የሚለውን ወያኔ የኢትዩጵያ ህዝብ ከስሩ መንግሎ መጣል በሃገር የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ ነው፡፡ ዘውጌኛ የትግራይ፣የሶማሌ ወዘተ ጠባብ ብሄረተኛነት በሰፊ ኢትዩጵያዊ ብሄረተኛነት መተካት አለበት፡፡ በሕወሓት በተቀናበረው ሴራ፣ የሱማሌ የጦር አበጋዞች በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሱት አደጋ፣ የሞት፣ የስደት፣ የመፈናቀል፣ የእርስ በእርስ ጦርነት ጥቃቶች አብሮ በኖረው ህዝብ ዘንድ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያልፋል፡፡ የወያኔ የፖለቲካ ሴራ ተጋልጦ የሱማሌና የኦሮማ ህዝብ አብረው ይኖራሉ፡፡ የህወኃት ጄነራሎች እነ ጄነራል አብርሃም ወልዴ (ካርተር) በሱማሌ ክልል ውስጥ ስውር መሪዎች በመሆን፣ አብዲ ኢሊ በመሾም  ልዩ የፖሊስ ኃይል በማደራጀት የፖለቲካ አይነኬዎች በመፍጠር  ከሱማሌ የጦር አበጋዞች ጋር ሽርክና መስርተዋል፡፡ የኢኮኖሚ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በኮንትሮባንድ ንግድ በተለይም በጮት፣ ማእድን ኃብት፣ የቁም እንሰሳትን ወዘተ በድንበር ዘለል ንግድ በማካሄድ የውጪ ምንዛሪ ዶላር በማከማቸት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ተቆጣጥረዋል፡፡ ለዘመናት አብረው የኖሩትን የሱማሌና የኦሮሞ ህዝብ በማጣላት ከሱማሌ ክልል የኦሮሞ ተወላጆችን በብዙ መቶ ሽህ የሚቆጠር ህዝብ ከኖረበት ቀየ እንዲፈናቀል አድርገዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ የእንቢተኝነት ትግልን ለማኮላሸት ህወኃት የጠነሰሰው ሴራ በመሆኑ የመከላከያ ሠራዊቱ ጣልቃ አልገባም፣ እንዲውም ከፍተኛ የኦህዴድ አመራሮች ከግድያ ሙከራ አምልጠዋል፡፡  የህወኃት በትረ ሥልጣኑን የማቆየት አንዱን ብሄር ከሌላው በማጋጨት በተለይም የአማራና የኦሮሞ ህዝብን በማጣላት ስልቱ ከሽፎበታል፡፡ በዚህም የተነሳ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት በምድረ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የሱማሌ የጦር አበጋዞች መንግስት በመፈልፈል የአናሳ ብሄራት ህብረት በመፍጠር፣ ለልዩ ፖሊስ ኃይል መሣሪያ በማሳታጠቅ የኦሮሞ ህዝብ ላይ በማዝመት ታሪክ ይቅር የማይለው በደል በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡ በሌሎችም የኢትዩጵያ ክልሎች ተመሳሳይ የጦር አበጋዞች መንግስት፣ በህወኃት መፈጠራቸው አይቀሬ ነው፡፡
{1} የጦር አበጋዝ ማለት የግል ወታደራዊ ኃይል በማደራጀት፣ ለግል ጥቅም ስልጣንና ኃብትን የሚያካብት ተዋናይ ሲሆን በአንድ ሃገር፣ያለው መንግስትና መንግስታዊ መዋቅሮች ጠንካራ ባልሆነበት አካባቢ የሚፈለፈል የጦር አበጋዝ ነው፡፡(ማኪንሌይ፣2007)‘Warlord’ is a term which used to describe a specific period of China’s history but which has re-emerged as a label during the last three decades (MacKinlay, 2007). The definition of a warlord differ, but most authors agree that a Warlord is an actor who accumulate power and wealth for private means by using military force in an environment where the formal state has little or no control (Reno, 1998, MacKinlay, 2007). በኢትዮጵያ ወታደራዊው መንግስት ሲዳከምና በየቦታው ከአማፂያን ጋር ጦርነት ሲገጥም ድንበር ላይ ያሉ ግዛቶች የሚያገናኛቸው መስረተ ልምት መንገድ፣ ባቡር ወዘተ ያልዘመነ በመሆኑ ምክንያት የመንግስት ሥልጣንና ኃላፊነት እየተዳከመ ሲሄድ ቀየው በአካባቢው በሚገኙ የጎሳ የጦር አበጋዞች (የጎበዝ አለቃዎች) ህወኃት፣ሻብያ፣ኦነግ ወዘተ ቁጥጥር ስር ወደቀ፡፡ በዚህም መሠረት በኢትዩጵያ ታሪክ ከ1960 እስከ ከ2010ዓ/ም እስካሁን ያለው አገዛዝ የወያኔ ‹‹ዘመነ-ጦር አበጋዞች  መንግስት›› እንደ አሸን የተፈለፈሉበት ዘመን  እንደሆነ ጥናታዊ ፁሁፉ ያስረዳል፡፡
2} ‹‹የፖለቲካ የማንነት ጥያቄ›› Identities Politics
በአፍሪካ የዘመነ-ጦር አበጋዞች ‹‹የማንነት ጥያቄ›› ዘውጌ ብሄረተኛነት ፅንሰ ሃሳብ ዋነኛና አንገብጋቢ የፖለቲካ ጥያቄ የሆነው ለዚህ ነው፡፡ ዘውጌ ብሄረተኛነት፣‹‹በማህበራዊ ጭብጦች ላይ ሳይሆን፣ በዝርያ፣ በወገን መመሳሰል ላይ የተመሠረተ ብሄርተኛነት››ነው፡፡ (አንዳርጋቸው ፅጌ ገፅ310) በዘመነ-ጦር አበጋዞች በጎሳ፣ በነገድ፣ በዘር፣ በዘውግ፣ በክልል (የደም ግንኙነት፣ የዘር ሃረግ፣ የቌንቌ፣ ወዘተ) ላይ የተከለሉና የተመሠረቱ አንድ ዘርን  በውትድርና በማሠልጠን፣ በማደራጀትና ተዋጊዎች በመመልመልና በሌሎች ዘሮች ላይ በማስነሳት፣የፖለቲካ ሥልጣን ለመጨበጥ የማንነት ጥያቄን ሽሮ መብሊያቸው አደረጉት፡፡ ማርክሲዝም ሌኒኒዝም፣ ማኦይዝም ቀመስ የሆኑ የጦር አበጋዞች በስመ ሶሻሊዝም የብሄር ብሄረሰብን ጥያቄ በማራገብ የጀሌውን ደቀ መዝሙር ህሊና አጠቡት፡፡ የጦር አበጋዞቹ እልፍ አእላፍ ገበሬዎችን በወታደርነት በመመልመልና አንዱን ዘር በሌላው ዘር ላይ ጥላቻ በመቀስቀስ፣ የራሳቸውን ታማኝ ጦር ማደራጀት ቻሉ፡፡ የጦር አበጋዞቹ  የማንነት ጥያቄ ኢንተርፕሬነር ፈላስፎች ሆኑ፡፡

No comments:

Post a Comment