Friday, September 15, 2017

በምእራብ ጉጂ ዞን በደቡብ ኮንሶ አዋሳኝ ድንበር ላይ ያካባቢዉ አርሶ አደር ከልዩ ኃይል ፖሊሶች ጋር ከፍተኛ ዉጊያ ላይ ነው


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |


 


በምእራብ ጉጂ ዞን በደቡብ ኮንሶ አዋሳኝ ድንበር ላይ ያካባቢዉ አርሶ አደር ከልዩ ሐይል ፖሊሶች ጋር ከፍተኛ ዉጊያ ላይ መሆኑን ከስፍራዉ የደረሰን ዜና አመለከተ።
አራት ሰዎች መሞታቸዉ እና ሰባት መቁሰላቸዉም ታዉቋል::

ያይን እማኞች እንደሚሉት ትላንት መስከረም 4 ማምሻዉ ላይ በጀመረዉ ዉጊያ ሌሊቱን የከባድ መሳሪያ ድምፅ የታከለበት ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ ማደሩን እና ከነጋ በኋላም ድንበር ላይ በምትገኝዉ ሀገረማርያም ወይንም ቡሌ ሆራ ከተማ ዉስጥ በመዝለቅ በነዋሪዎች ላይ ታጣቂዎች ሲተኩሱ እንደነበርም ተናግረዋል፡ል አክለዉም ትላንት ለሊት 4 ሰዎች ካርሶአደሮች መሞታቸዉን እና 7 ሰዎች መቁሰላቸዉን፣ የቡሌ ሆራ ሆስፒታልም በቁስለኛች ተጨናንቆ እንደሚገኝ፤ግማሹ ቁስለኛም ወደ ዲላ ሆስፒታል እየተጫነ መሆኑን ፣እንዲሁም ከገጠር ቀበሌዎችም ዛሬ ረፋዱ ላይ ቁስለኞች ወደ ሁስቲታሎች እየገቡ መሆናቸዉንም ጠቅሰዋል።
ታርጋ ቁጥር 0241 እና 0252 የሆኑ የኦሮሚያ ፖሊስ መከላከያ ፒካፕ ተሽከርካሪዎች፤ ለልዩ ሐይል ታጣቂዎች መሳሪያን እና ስንቅን ጨምሮ የሚያስገልጋቸዉን ግብአቶች እየተመላለሱ ሲያቀብሉ መታየታቸዉንም ባካባቢዉ የነበሩ ያይን እማኞች ሲናገሩ፤በሌላ በኩል የአገዛዙ አባላት ጥቃቱን እየፈፀሙት ያሉት በድንበር ግጭት ሰበብ የኮንሶ ተወላጆች እንደሆኑ ለማስመሰል ሙከራዎች እያደረጉ እንዳለ ጠቅሰዋል። ሆኖን ያካባቢዉ አርሶ አደር እና ነዋሪ ጥቃቱን እየፈፀመ ላለዉ እና የህዉሀት አገዛዝ ጉዳይ አስፈፃሚ ነዉ ሲሉ ለሚቀሱት ልዩ ሀይል በመተባበር ምላሽ እየጡ መሆናቸዉን ገልፀዋል።
መረጃዉ ለዝግጅት ክፍላችን እስከደረሰበት ግዜ ድረስ በሐገረማርም ወይን በቡሬ ሆራ ከተማ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደሌለ እና በመንገድ ላይ ከልዩ ሀይሎች እና ከእንስሳት በስተቀር ነዋሪዉ ሁሉ ቤቱን ዘግቶ በፍርሀት ተዉጦ እንደሚገኝም ገልፀዋል። የመኪና መንገድን እስከሞያሌ ድረስ ተዘግቶ እንደሚገኝም ነዉ የገለፁት።
የህዋት አገዛዝ ከተፈጠረበር ዉጥረት ጥቂት ፋታ ለማግኘት በሀገሪቱ ዉስጥ ያለዉን የተለያየ ብሔር እርስበርስ በመከፋፈል ስራ ተጠምዶ እንደሚገኝ እና ጦርነቶችን በየክልሉ እየፈጠረ እንዳለ በመረዳት በጋራ መቆን እንዳለባቸዉ የሀገር ሽማግሌዎች መልክትን እ ስተላለፉ እንዳለም ተናግረዋል::
ምንጭ: ትንሳኤ ራድዮ

No comments:

Post a Comment